በአዲስ አበባ የመሶብ ቅርፅ ያለው ባለ 70 ወለል ሕንፃ ሊገነባ ነው

0
611

እስከ ስድስት ዓመት ድረስ ይገነባል የተባለው ሕንፃ ባለቤት የባሕልና ቱሪዝም ሚንስቴር ሲሆን፣ የመሶብ ቅርጹ የተመረጠው የኢትዮጵያዊያንን የአብሮነት፣ የመሰባሰብ፣ የጋራ ደስታና ቃልኪዳን ምሳሌነትን ይወክላል በሚል ነው ተብሏል።
ሚንስቴሩ የሚያሠራው ባለ 70 ወለል ሕንፃ 250 ሜትር ከፍታ እንደሚኖረው ተነግሯል። ይሕም በምሥራቅ አፍሪካ ረጅሙ ሕንፃ ሊያደርገው እንደሚችል ተገምቷል። ለግንባታውም ከ50 ሺሕ ካሬ ሜትር በላይ ቦታ ይፈለጋል የተባለ ሲሆን ሕንጻው በ20 ሺሕ ካሬ ሜትር ላይ እንደሚያርፍ ተጠቁሟል።
ሕንጻው እውን ሲሆን ባሕላዊና ዘመናዊ ሆቴሎች፣ የገበያ ማዕከላት፣ ክልሎችን የሚወክል የባሕል ማዕከል፣ የጎልፍ ሜዳ፣ የተለያዩ የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎችና የቱሪዝምና ሆቴል ማሰልጠኛ ማዕከል እንደሚኖረው ተነግሯል።
ሕንጻውን ለመገንባት ዝግጅት መጀመሩን የጠቀሰው ሚኒስቴሩ ከአጋሮቹ ጋር እየመከረበት ስለመሆኑ ጠቁቋል።
ስለሚፈጀው በጀትና የግንባታ ቦታው የተጠየቀው ሚንስቴሩ ምክክሬን ስጨርስ በምሰጠው መግለጫ ይፋ አደርጋለሁ ብሏል።

ቅጽ 1 ቁጥር 7 ታኅሣሥ 20 ቀን 2011

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here