የጣና ፎረም አጀንዳ ፀደቀ

0
469

ዘንድሮ ለ8ኛ ጊዜ የሚካሔደውና በአፍሪካ የደኅንነት ጉዳዮች ላይ የሚያተኩረው የጣና ከፍተኛ ባለስልጣናት ስብሰባ አጀንዳ ፀደቀ።
በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የሠላምና ደኅንነት ጥናት ተቋም አዘጋጅነት በየዓመቱ ባሕር ዳር ላይ የሚካሄደው የጣና ፎረም ‹‹የፖለቲካ ሁኔታ ተለዋዋጭነት በአፍሪካ ቀንድ፤ የሠላም ጅማሮዎችን ማስቀጠል›› በሚል አጀንዳ በመጭው ሚያዚያ የመጨረሻ ቀናት ይካሄዳል።
የዘንድሮው አጀንዳም በጠቅላይ ሚንስትር ጽሕፈት ቤት ፀድቋል። ከዚህ ቀደም በተካሔዱት ሰባት ስብሰባዎች እና በቀረቡ ጥናቶች በመመርኮዝ የፖሊሲ ማጎልበት ሥራ እየተሰራ እንዳለ ታውቋል።
የአፍሪካ ቀንድን የፖለቲካ ሁኔታ ማዕከል አድርጎ ውይይቱን ያካሂዳል ተብሎ የሚጠበቀዉ 8ኛው የጣና ፎረም ከቀድሞዎቹ በተለየ አህጉራዊ ጉዳዮች ይዳሰሱባታል፤ ለፖለቲካዊ ችግሮችም መፍትሔ ይበጅበታል ተብሎ ይጠበቃል።
በአውሮፓዊያኑ 2012 በቀድሞ ጠቅላይ ሚንስትር መለስ ዜናዊ፣ የቀድሞው የናይጀሪያ ፕሬዚደንት ኦሊሴ ጎን ኦባሳንጆን እና በሌሎች የአፍሪካ ከፍተኛ ምሑራን መጀመሩ ይታወቃል።

ቅጽ 1 ቁጥር 7 ታኅሣሥ 20 ቀን 2011

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here