በአፋር በጎርፍ በተጠቁ አካባቢዎች የሚገኙ ተማሪዎችን ወደ ትምህርት ገበታ ለማምጣት እየተሰራ ነው

0
727

በአፋር ክልል ገጠር ቀበሌዎች ከጥቅምት 9 /2013 ጀምሮ ትምህርት እንደ ተጀመረ እና በከተሞች በሚገኙ ትምህርት ቤቶች ደግሞ ጥቅምት 16/2013 እንደሚጀመር ይጠበቃል።
በጎርፍ በተጠቁ አካባቢዎች የሚገኙ 105 ትምህርት ቤቶችን ፈጥኖ ወደ ስራ ለማስገባት ባለመቻሉ ተቋቅማቱን ትምህርት የማስጀመሪያ ጊዜ መራዘሙን ተገልጿል።
ከትምህርት ቤቶቹ ውስጥ 58ቱ ሙሉ ለሙሉ በውሀ የተዋጡ ፣ 18ቱ በውሀ የተከበቡ እንዲሁም 29ኙ በጎርፍ የተፈናቀሉ ነዋሪዎች የተጠለሉባቸው ናቸው።
በትምህርት ቤቶቹ የሚኖሩ 41 ሺህ 169 ተማሪዎችን ወደ ትምህርት ገበታ ለማምጣት እየተሰራ ነው።
በጎርፍ ጉዳት በደረሰባቸው ትምህርት ቤቶች ምትክ የዳስና የቆርቆሮ ክፍሎችን በመገንባት ተማሪዎቹን ጥቅምት 30 ቀን 2013 ዓም ትምህርት ለማስጀመር እየተሰራ መሆኑም ተገልጿል።
የትግራይ ህዝብ ጥያቄ ምላሽ እንዲያገኝ የሚያስችል ህጋዊ አሰራር እየተዘጋጀ እንደሚገኝ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አስታወቀ፡፡

ቅጽ 2 ቁጥር 103 ጥቅምት 14 2013

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here