የፌደራል ኅብረት ሥራ ማኅበራትን ኤጀንሲ እንደ አዲስ ሊደራጅ ነው

0
1352

የፌደራል ኅብረት ሥራ ኤጀንሲ በኢትዮጵያ ያሉ ኅብረት ሥራ ማኅበራትን አሁን ላይ በደረሱበትና ወደፊት በሚደርሱበት ደረጃ ልክ እንደ አዲስ ለማደራጀት እቅድ መያዙን አስታወቀ።

ማኅበሩ ለአዲስ ማለዳ እንዳስታወቀው በመላው አገሪቱ በስሩ የሚገኙ ኅብረት ሥራ ማኅበራትን አሁን በደረሱበት እና ወደፊት ለሚደርሱበት ደረጃ መጣኝ በሆነ መለኩ በየደረጃው ለማደራጀት እና የማኅበራቱን አቅም በማሳደግ በአገሪቱ አጠቃላይ ንግድ እንቅስቀሴ ውስጥ የሚኖራቸውን ድርሻ ለማሳደግ መሆኑ ተገልጿል።

የኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር ዑስማን ስሩር ከአዲስ ማለዳ ጋር በነበራቸው ቆይታ የኢትያጵያ ኅብረት ስራ ማኅበራት የደረሱበት የእድገት ደረጃ ያገናዘበ ማኅበራትን ማደራጅት አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ ኅብረት ሥራ ማኅበራትን በየዘርፉ በደረጃ ማደራጀት አስፈላጊ ነው ብላዋል። ዳይሬክተሩ አክለውም በኢትዮጵያ የኅብረት ሥራ ማኅበራት እድገት ደረጃው በማኅበራት ቁጥር፣ በአባላት ብዛትና በፈጠሩት ሀብት እድገታቸውና አደረጃጀታቸው አለመጣጠኑን ተናግረዋል።

“አሁን የተፈጠሩት ኅብረት ሥራ ማኅበራት በደረደሱበት የእድገት ደረጃ በአሰራር፣ በአደረጃጀትና በሰው ሀይል ልክ ካልተደራጁ እድገቱ ባለበት ቆሞ ይቀራል ማለት ነው። ስለዚህ ዛሬ የኢትዮጵያ ኅብረት ስራ ማኅበራት በደረሱበት ደረጃ መደራጀት ያፈልጋል።” ሲሉ ለአዲስ ማለዳ ተናግረዋል።

የኅብረት ሥራ ማኅበራት ሴክተሩ እድገቱ በህብረተሰቡ፣ በመንግስትና በተቋማት በኩል ፍላጎቱ እያደገ ነው ያሉት ዑስማን አሁን ያለውን ፍላጎትና እድገት ያገናዘበ ተቋማዊ አደረጃጀት ያስፈልጋል ብለዋል። ተቋማዊ ለውጡ በተጠናከረ ደረጃ ሲገነባ አሁን ያለውን የመንግስትን፣ የአባላትንና የህብረተሰቡን ፍላጎት መመለስ ይቻላልም ብለዋል።

አሁን ላይ በኢትዮጵያ ካሉት ኅብረት ሥራ ማኅበራት ውስጥ 50 ዎቹ ምርታቸወን ለዓለም ዓቀፍ ገብያ እያቀረቡ ሲሆን፣ እነዚህ ማኅበራት ምርታቸውን ለውጭ ገበያ ከሚያቀርቡ ዓለም ዓቀፍ ተቐማት ጋር ተወዳዳሪ በማድረግ የማኅበራቱን አቅምና ተወዳዳሪነት ለማጎልበት በአሰራር፣ በአደረጃጀትና በሰው ሀይል በተሻለ አቅም ማደራጅት አስፈላጊ መሆኑን ዑስማን ገልጸዋል።

ውጤታማ የሆነ አደረጃጀት ለመፍጠር አሁን በተለያያ ደረጃ ላይ የሚገኙትን 92 ሺሕ ኅብረት ሥራ ማኅበራት በየደረጃ እና በየዘርፉ እንደሚደራጁ ተመላክቷል። ዑስማን ለአዲስ ማለዳ እንዳስረዱት ከእነዚህ ማኅበራት ውስጥ በዓመት ከ 1.5 አስከ 3 ቢሊዮን ብር የንግድ እንቅስቃሴ የሚደርጉ እንዳሉ ሁሉ በአንጻሩ ደግሞ በዓመት ከ10 ሺሕ አስከ 20 ሺሕ ብር የሚንቀሳቅሱ አሉ ያሉት ዑስማን እንዚህን እንደየ ስራ ዘርፋቸው ከፍተኛ፣ መካከለኛ፣ ዝቅተኛና ከዝቅተኛ በታች ብሎ በደረጃ ማስቀመጥ አንዱ የሪፎርሙ አካል ነው።

በሌላ በኩል አደረጃጀቱን የሚያጠናክር መመሪያ ማዘጋጀት ሌላኛው የአዲሱ አደረጃጀት አካል ነው ተብሏል። መመሪያው ሲዘጋጅ የማኅበራትን ደረጃ በሚመጥን መልኩ ማዘጋጀት አስፈላጊ መሆኑን ዑስማን ገልጸዋል። በሰው ሀይል በኩል እያንዳንዱ ሰራተኛ በሰራው ሥራ ልክ ተጠቃሚ ማድረግ ተገቢ በመሆኑ በሪፎርሙ የሰራተኛ ደመወዝና ጉርሻ በሪፎርም እንደሚካተት ዳይሬክተሩ ለአዲስ ማለዳ ጠቁመዋል።

እንዲሁም ማኅበራት በሳይንሳዊ አስራርና በሙያተኛ መመራት የሚችሉበትን አሰራር እንደሚፈጠርም ነው ዳይሬክተሩ አክለው የጠቆሙት፡ የኅብረት ሥራ ማኅባራት አሁን ባለው ሁኔታ ምርታቸቀወን ለውጭ ገበያ እያቀረቡ ሲሆን የአደረጃጃት ለውጡ የውጭ ንግድ ተሳትፎ ለማሳድግ የሚሰራው ሥራ አካል መሆኑን የኤጀንሲው ዳይሬክተር አመላክተዋል። አደረጃጃቱ ሲጠናከር ዓለም ዓቀፍ ደረጃ የተወዳዳሪ ተቋማት አቅም መጎልበት እንደሚጠበቅም ዳይሬክተሩ አክለው ገልጸዋል። በውጭ ንግድ አስካሁን ያልተሰራባቸው እንደ ቅመማ ቅምም፣ አትክልና ሌሎችም በኅብረት ሥራ ማኀበራት ዘርፍ የተሻለ ለመስራት ጥረት እየተደረገ መሆኑን ዑስማን አብራርተዋል።

የፌደራል ኅብረት ሥራ ኤጀንሲ ቁጥር 92 ሺሕ የደረሰ ሲሆኑ፣ አጠቃላይ ማኅበራት አባላት ብዛት 22.5 ሚሊዮን ደርሷል። የማኅበራቱ አጠቃላይ ሀብት በአሁን ወቅት48 ቢሊዮን ብር ደርሷል ። የኅብረት ሥራ ማኅበራት በገሪቱ አጠቃለይ ገብያ እንቅስቃሴ ላይ 15 በመቶ ድርሻ አላቸው።

ቅጽ 2 ቁጥር 103 ጥቅምት 14 2013

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here