በደብረ ብረሃን ከተማ አስተዳደር በተያዘው 2013 በጀት ዓመት የተለያዩ 39 የመሰረተ ልማት ሥራዎችን ለማስፋፋት 171 ሚሊዮን ብር ወጭ ሊገነቡ መሆኑን ደብረ ብርሃን ከተማ አስተዳደር ቤቶች ግንባታና አገልግሎት ጽፈት ቤት አስታወቀ።
በ2013 በከተማው ለሚገነቡ መሰረተ ልማቶች ከ171 ሚልዮን ብር በላይ በጀት መያዙን ያስታወቀው የደብረ ብርሃን ከተማ አስተዳደር ቤቶች ግንባታና አገልግሎት ጽህፈት ቤት ለአዲስ ማለዳ እዳስታወቀው ፕሮጀክቶቹን ለማስፈጸም ከተያዘው 171 ሚሊዮን ብር ውስጥ 67 ሚሊዮን ብር ከዓለም ባንክ በድጋፍ የተገኘ ነው ተብሏል።
ቀሪውን 75 ሚሊዮን ብር ከተማ አስተዳደሩ የሚሸፈግን ሲሆን 29 ሚሊዮን ብር የአማራ ክልል መንግስት እንደሚሸፍን የደብረ ብርሃን ከተማ አስተዳደር ቤቶች ግንባታና አገልግሎት ጽ/ቤት የግንባት ዘርፍ ሥራ አስኪያጅ መኮንን አሻው ለአዲስ ማለዳ አስረድተዋል።
በ171 ሚሊዮን ብር ከሚሰሩ የመሰረተ ልማት ፕሮጀክቶች ውስጥ በዋናነት የመንገድ ግንባታ እና ዘመናዊ የቆሻሻ ማስወገጃ ፕሮጀክቶች ትልቁን የበጀት ድረሻ እንሚይዙ መኮንን አብራርተዋል። ዘመናዊ የደረቅ ቆሻሻ ማስወገዳ ፕሮጀክቱም 126 ሚሊዮን ብር እንደተያዘለት ተመላክቷል።
መኮንን አክለውም በበጀት አመቱ ሊገነቡ የተያዙት የመሰረተ ልማት ግንባታዎች 2 ነጥብ 4 ኪሎ ሜትር የኮብል መንገድ፣ 4ነጥብ 6 ኪሎ ሜትር የጠጠር መንግድ እና የመንገድ ተፋሰስ፣ ጊዘያዊ የደረቅ ቆሻሻ ማሸጋገሪያ፣ የመብራት ዝርጋታ፣ የውሃ ማስፋፊያ፣ የመንገድ ዳር አረንኋደ ልማት(መናፈሻ ግንባታዎችን ያካተተ)፣ ዘመናዊ የደረቅ ቆሻሻ ማስወገጃና የስፖርት ማዘውተሪያ ግንባታዎች በዋናነት የሚጠቀሱ መሆናቸውን ጠቁመው ካሁን ቀደም የተሰሩ ጥገና የሚያስፈልጋቸው መሰረተ ልማቶችንም ለመጠገን በእቅዱ የተካተቱ መሆናቸውን ተናግረዋል።
መኮንን ለአዲስ ማለዳ አንዳስረዱት ከዚህ ቀደም ተሰርተው ጥገና ለሚስፈልጋቸው መሰረት ልማቶች ከ171 ሚሊዮን ብር ውጭ 14 ሚሊዮን ብር በጀት መያዙን ተቁመዋል።
በከተማዋ በተያዘው በጀት ዓመት ሊገነቡ በጀት የተያዘላቸው ፕሮጀክቶችን ለማስጀመር ጽ/ቤቱ ፕሮጀክቶቹን ለሚከውኑ ኢንተርፕራዩዞች ለማስተላለፍ ጨረታ አውጥቷል።በበጀት ዓመቱ ሊገነቡ በጀት ከተያዘላቸው 39 ፕሮጀክቶች ውስጥ 28ቱ ለጥቃቅንና አነስተኛ የሚሰጡ ናቸው።
ፕሮጀክቶቹን የሚረከቡ 29 ኢንተርፕራይዞች ተደራጅተውና ስልጠና ወስደው ወደ ሥራ ሊገቡ ዝጉጁ መሆናቸውን ለአዲስ ማለዳ የገለፁት ደግሞ የደብረ ብርሃን ከተማ አስተዳደር ቴክኒክና ሙያ ኢንተርፕራይዝ ልማት ጽ/ቤት ምክትል ኃላፊ ውብሸት የሺዳኘ ናቸው። ምክትል ኃላፊው ለአዲስ ማለዳ እንደገጹት 28 አዲስ ኢንተርፕራይዞች በጠቅላላ ሥራ ተቋራጭ ተደራጅተው በፕሮጀክት ሥራዎች ላይ ለመሳተፍ የጨረታ ሰነድ መሙላታቸወን አመላክተዋል።
በተጨማሪም በከተማዋ ከሚገነቡ የመሰረተ ልማት ግንባታዎች ውስጥ የ20 በመቶ ድረሻ ወስደው በፕሮጀክት ግንባታዎች ላይ የሚሳተፉ 11 ነባር ኢንተርፕርይዞች መኖራቸውን ውብሸት ጠቅሰዋል። ለፕሮጀክት ግባታዎች የተደራጁ ኢንተርፕራይዞች እያንዳንዳቸው በስራቸው ከ7 እስከ 12 የሰው ኃይል አላቸው ተብሏል።
በሌላ መኩል በደብረ ብርሃን ከተማ በዓለም ባንክ የሚደገፍ የመሬት ምዝግባ ፕሮጀክት በ3 ሚሊዮን ብር ወጭ በበጀት ዓመቱ እንደሚከናን ውብሸት ጠቁመዋል። ለፕሮጀክቱ አራት ኢንተር ፕራይዞች ቴክኒካል ስልጠና ወስደው ዝግጁ መሆናቸው ተመላክቷል።
ደብረ ብርሃን ካለፈው 2012 ጀምሮ የኢንቨስትመንት አማራጭ መዳረሻ እየሆነች የምትገኝ ከተማ ናት። በ2013 በጀት ዓመት በከተማዋ በተለያየ የኢንቨስትመንት ዘርፍ 4.1 ቢሊዮን ብር ካፒታል ላስመዘገቡ 74 ባለሀብቶች የኢንቨስትመንት ፈቃድ ሰጥታለች። እንደ ደብረ ብርሃን ከተማ ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት ፅ/ ቤት መረጃ በተሰጠው የኢንቨስትመንት ፈቃድ ለ13 ሺሕ 532 ቋሚ እና ጊዜያዊ የሥራ እድል ይፈጥራሉ ተብሏል።
ቅጽ 2 ቁጥር 103 ጥቅምት 14 2013


