ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ አዲስ መተግበሪያን ይፋ አደረገ

0
746

ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ የኅብረተሰቡን ተደራሽነትን ለማስፋት አዲስ መተግበሪያን ዓርብ፣ ታኅሣሠ 19 ይፋ አደረገ።
አዲሱ የመረጃ ቋትን የያዘው መተግበሪያ በሕግና ተያያዥ ጉዳዮች ላይ መረጃዎችን ለማግኘት ጉልህ አስተዋፅኦ ያደርጋል የሚል ተስፋም ተጥሎበታል። መተግበሪያው ከ1934 እስከ 2010 ድረስ ያሉ ሕጎችን፣ አዋጆችን፣ ደንቦችንና የሰበር ውሳኔዎችን አካቶ የያዘ የመረጃ ቋት ነው ተብሏል። ይህ መተግበሪያ የበይነ መረብ አገልግሎት በማይገኝባቸው ቦታዎችም ለተጠቃሚዎች መረጃ ማግኘት የሚያስችል መሆኑም ተነግሮለታል።
የመረጃ ቋት መተግበሪያውን ተንቀሳቃሽ ስልኮችን ጨምሮ በሌሎች የኤሌክትሮኒክስ መሣሪያዎች ላይ በመጫን መጠቀም ይቻላል። መተግበሪያው የተለያዩ ሕጎች ሲሻሻሉም በራሱ ጊዜ የመረጃ ቋቱን እንደሚያሻሽልና በአዲስ እየተካ እንደሚሄድ ተነግሮለታል።
ጠቅላይ ዐቃቤ ሕጉ ብርሃኑ ጸጋዬ እንዳሉት የአሠራር ሒደቱን ለማዘመን በማሰብ የቀረበው መተግበሪያ ኢትዮጵያ ለ53 ዓመታት የነበሯትን የተለያዩ የሕግ ማዕቀፍ ሰነዶች ለተጠቃሚዎች በቀላሉ እንዲደርሱ የሚረዳ ነው።

ቅጽ 1 ቁጥር 7 ታኅሣሥ 20 ቀን 2011

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here