ኮርፖሬሽኑ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 5 ቢሊየን ብር ሊበደር ነው

0
212

የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽን የጀመራቸውን ፕሮጀክቶች ለማጠናቀቅ ከንግድ ባንክ 5 ቢሊየን ብር ሊበድር እንደሆነ አስታወቀ።
ኮርፖሬሽኑ የግድብ እና መስኖ ልማት ዘርፍን ለማጠናቀቅ ብድር ሊወስድ እንደሆነ አስታውቋል። ከነዚህም መካከል የኩራዝ ፋብሪካ መስኖ ልማት ዘርፍ፣ የኩራዝ መስኖ ልማት ግንባታ ፕሮጀክት፣ የሞጆ ደረቅ ወደብ ግንባታ ምዕራፍ ሁለት እና ሦስት፣ የወልቃይት ስኳር ልማት መስኖ ፕሮጀክት እና አርጆ ዴዴሳ ስኳር ልማት መስኖ ፕሮጀክት ለመገንባት ርብርብ እያደረገ እንደሆነ የኮርፖሬሽኑ ሥራ አስኪያጅ ጥንፉ ሙጬ በተለይ ለአዲስ ማለዳ አስታውቀዋል።
በኮርፖሬሽኑ ውስጥ የሚገኘው ሕንፃ ቴክኖሎጂ ኮንስትራክሽን ዘርፍ 17 ፕሮጀክቶችን ይዞ የሚንቀሳቀስ ሲሆን ከእነዚህ ውስጥ 11 የተለያዩ አፈጻፀም ያላቸው ሲሆኑ ለብሔራዊ ባንክ 5 የሚያሠራቸው ሕንፃዎች ነበሩ። በተጨማሪም ዘርፉ ከሚያመርታቸው ውስጥ የበር እና የመስኮት፣ የኮንክሪት ውጤቶች ያመርታል እንዲሁም የብሎኬት ምርቶችን የሚያመርት ሲሆን የእነዚህም አፈፃፀም 47.8 ከመቶ መሆኑን አሳውቀዋል።
የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽን ግድብ እና መስኖ ፕሮጀክቶችን ለማስተዳደር እና ለመገንባት በስኳር ኮርፖሬሽንና ብረታ ብረት ይሰሩ የነበሩ አዳዲስ ግድቦችን እንዲገነባ ተልዕኮ ተሰጥቶት እንደነበር እና ይህንንም ፕሮጀክት ለመገንባት ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 9.6 ቢሊየን ብር መበደሩ ይታወሳል።
ኮርፖሬሽኑ እስካሁን ለተለያዩ ሥራዎች ለወሰዳቸው በገንዘብ ሚኒስቴር ዋስትና ብድሮች 441 ሚሊዮን ብር ወለድ ከፍሏል።

ቅጽ 1 ቁጥር 8 ታኅሣሥ 27 ቀን 2011

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here