ምንጭ፡-የዓለም ኢኮኖሚክ መድረክ
የዓለም ኢኮኖሚክ መድረክ በ2020 የዓለም አቀፍ የሥርዓተ-ፆታ ክፍተት(Global Gender Gap) ሪፖርቱ እንዳመለከተው በዓለም ዙሪያ የሚገኙ ከአንድ አምስተኛ እስከ ግማሽ ያህል የሚሆኑ ሴቶች ከወንድ አጋሮቻቸው አካላዊ ወይም ወሲባዊ ጥቃት እንደሚገጥማቸው አስታውቋል። እንደ ሪፖርቱም ከሆነ በመካከለኛው ምስራቅ እና በሰሜን አፍሪካ ውስጥ 45 በመቶ የሚሆኑት ሴቶች ጉዳት የደረሰባቸው በመሆናቸው ከፍተኛውን ደረጃ ይይዛሉ።
ችግሩ ግን በምስራቅ እና በሰሜን አፍሪካ ውስጥ ብቻ ሳይሆን በመላው ዓለም የቀጠለ እንደሆነም ተገልጿል። በሰሜን አሜሪካ ውስጥ የጥቃት መጠኑ 32 በመቶ ሲሆን በምዕራብ አውሮፓ ደግሞ 22% እንዲሁም በእንግሊዝ ውስጥ አንድ ወንድ በአገሪቱ ውስጥ በየሦስት ቀኑ አንድ ሴትን እንደሚገድል በአይነቱ የመጀመሪያ የሆነው የዳሰሳ ጥናት (Femicide Census) ዘገባ ያሳያል። ይህ ቁጥርም ለባለፉት 10 ዓመታት ያልተለወጠ አኃዛዊ መረጃ እንደሆነም ተገልጿል።
እንደ ጥናቱ ከሆነ በዓለም አቀፍ ደረጃ ከአጠቃላይ የሴቶች ቁጥር 31 በመቶ የሚሆኑት ሴቶች ፆታዊ ጥቃት ይደርስባቸዋል።
ቅጽ 2 ቁጥር 108 ኅዳር 19 2013



