የጃፓን መንግስት በጠመንጃ ያዥ ትምህርት ቤት ግንባታ ለማከናወን ተስማማ

0
728

የጃፓን መንግሥት በአዲስ አበባ ከተማ በቂርቆስ ክፈለ ከተማ በሚገኘዉ ጠመንጃ ያዥ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ውስጥ አምስት የመምህራን ክፍሎችና አንድ ቤተመጻሕፍት ለማስገንባት የሦስት ነጥብ አራት ሚሊዮን ብር ስምምነት ፈፀመ።
ስምምነቱን በኢትዮጵያ የጃፓን አምባሳደር ኢቶ ታካካ እና የትምህርት ቤቱ ርዕሰ መምህር አባተ ከልቤ ተፈራርመዋል።
የጃፓን መንግሥት ከ1989 ዓ.ም ጀምሮ በኢትዮጵያ እያካሄደ ያለው የሰው ልጆች ማኅበራዊ ዋስትና ፕሮጀክት አካል የሆነው ይህ ግንባታ በአንድ አመት ጊዜ የሚጠናቀቅ መሆኑም ተጠቁሟል።
በዚህ የሰው ልጆች ማኅበራዊ ዋስትና ፕሮጀክት አማካኝነት የጃፓን መንግሥት በትምህርት፣ በጤና፣ በንጹህ መጠጥ ውሃ፣ በንጽህና አጠባበቅ፣ በምግብ ዋስትናና በሌሎች የማኅበራዊ ዋስትና መስኮች ከ1989 ጀምሮ ከ400 በላይ የሚሆኑ ፕሮጀክቶችን አጠናቆ ማስረከቡን ከአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ የተገኘው መረጋ ይጠቁማል።

ቅጽ 2 ቁጥር 110 ታህሳስ 3 2013

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here