10ቱ ለንግድ ሥራ ምቹ የሆኑ አገራት

0
452

ምንጭ፡-(Doing Business Database)

የዓለም ባንክ በምንገኝበት በፈረንጆቹ 2020 ላይ በዓለማችን ለንግድ ሥራ ምቹ የሆኑ አገራት በማለት ባወጣው ደረጃ መሰረት ኒውዝላንድ፣ ሲንጋፖር እና ሆንኮንግ (ቻይና) ከአንድ እስከ ሦስተኛ ያለውን ደረጃ ሲይዙ ከአፍሪካ ደግሞ ሩዋንዳ 76.5 በመቶ ለንግድ ሥራ ምቹነት ውጤትን በማምጣት አንደኛ ደረጃን በመያዝ ከዓለም 38ተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጣለች። ሞሮኮ በ73.4 በመቶ ከዓለም 53ተኛ ከአፍሪካ 2ተኛ ስትሆን ኬንያ ደግሞ በ73.2 በመቶ ውጤት ከዓለም 56ተኛ ከአፍሪካ 3ተኛ ደረጃን በመያዝ ትከተላለች።
አገራችን ኢትዮጵያም በደረጃ ሰንጠረዡ ላይ 48.0 በመቶኛ ለንግድ ሥራ ምቹነት ውጤትን በማስመዝገብ ለስራ ምቹ ከሆኑ አገራት ውስጥ የ159ኛ ደረጃን ይዛለች። የግንባታ ፍቃዶችን በመስጠት፣ የህንፃ ጥራት ቁጥጥርና የግንባታ ባለሙያዎችን ብቃት ማጠንከር ላይ መሻሻሎችን ማሳየቷንም መረጃው ያመለክታል።

ቅጽ 2 ቁጥር 110 ታህሳስ 3 2013

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here