205 ተጠርጣሪዎች በሕግ ቁጥጥር ሥር ውለዋል
በደቡብ ብሔር ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች ክልል ኮንሶ ዞን በተፈጠረው ግጭት የ68 ንጹሀን ዜጎች ሕይወት መጥፋቱን የክልሉ የሰላምና ጸጥታ ቢሮ ለአዲስ ማለዳ አስታወቀ፡፡
በደቡብ ክልል ኮንሶ ዞን በሦስት ወረዳዎች በሚገኙ ቀበሌዎች ባሳለፍነው ኅዳር 6/2013 ተፈጥሮ በነበረው ግጭት 68 ንጹሐን ዜጎች ሕይወታቸውን ማጣታቸውን ለአዲስ ማለዳ የገለጸው የክልሉ ሰላምና ጸጥታ ቢሮ 49 ሰዎች የአካል ጉዳት ደርሶባቸዋል ብሏል፡፡ በግጭቱ ከሰው ሕይወት ሕልፈት በተጨማሪ የንብረትና የእንሰሳት ውድመት መከሰቱን የክልሉ ሰላምና ጽጥታ ቢሮ ኀላፊ አለማየሁ ባውዲ ለአዲስ ማለዳ ተናግረዋል፡፡
ኀላፊ ው ለአዲስ ማለዳ እንዳስታወቁት በግጭቱ ከአምስት ሺሕ በላይ ሳር ቤቶች እና ከ500 በላይ ቆርቆሮ ቤቶች መቃጠላቸውን ገልጸዋል፡፡ ጉዳቱ የደረሰው አጥቂ ቡድኖች ተደራጅትው ባደረሱት የአፈናና ሀብት ዘረፋ መሆኑን ኀላፊው ጠቁመዋል፡፡
“የተደራጀው አጥቂ ቡድን በአሰቃቂ ሁኔታ ሴቶች እና ሕጻናትን ገድሏል፣ ሬሳ አቃጥሏል” ሲሉ ሁኔታውን የገለጹት የክልሉ ሰላምና ጸጥታ ኀላፊ ድርጊቱ በአካባቢው ማኅበረሰብ ላይ የሕይወትና የሽነ ልቦና ቀውስ ፈጥሯል በለዋል፡፡ በዚህም በተፈጠረው ግጭት ከቤት ንብረታቸው ከተፈናቀሉት ከ100 ሺሕ በላይ ዜጎች 49 ሺሕ በአካባቢቸው ምንም ግጭት ሳይፈጠር በስጋት ቤት ንብረታቸውብን ትተው እንዲሸሹ ምክንያት መሆኑን ኀላፊው ጠቁመዋል፡፡
በግጭቱ ተፈናቅለዋል የተባሉት 49 ሺሕ በላይ ዜጎች ወደ አካባቢያቸው ተመልሰው መደበኛ ኑሯቸውን በመከወን ላይ መሆናቸውን ኀላፊው የገለጹ ሲሆን መጠነኛ ጥቃት ደርሶባቸው የተፈናቀሉ አምስት ሺሕ ዜጎች የወደሙ ቤቶችን ሥራ በመወጠር እና ሙሉ በሙሉ ያልወደሙተን ቤቶች እድሳት በማድረግ መመለስ መቻሉን ተናግረዋል፡፡ ቀሪዎቹ 50 ሺሕ የሚጠጉ ጌዞችን እስካሁን ወደ ቀያቸው እንዳልተመለሱም ተመላክቷል፡፡
የቢሮ ኀላፊ ው እንደሚሉት በግጭቱ ተጎጅ ሆነው ከቤት ንብረታቸው ተፈናቅለው እስካሁን በማቆያ ማዕከላት የሚገኙ ዜጎችን ወደ ቀያቸው ተመልሰው አዝመራቸውን የመሰብሰብ ፍላጎት ቢኖራቸውም እስካሁን አልተቻለም፡፡
የሕዝቡ ጥያቄ ወደ ቀየው መመለስ እና “ አዝመራየን ሰብስቤ ቀጣይ እጣ ፋንታየን ልወስን” የሚል መሆኑን ኀላፊው ለአዲስ ማለዳ አብራርተዋል፡፡
በንጹሐን ዜጎች ከፍተኛ ጉዳት አድርሰዋል የተባሉ 205 ተጠርጣሪዎች በሕግ ቁጥጥር ሥር መዋላቸውን የቢሮ ኀላፊ ው ለአዲስ ማለዳ አረጋግጠዋል፡፡ ተጠርጣሪዎቹ በሕግ ቁጥጥር ሥር የዋሉት በማኅበረሰቡ እገዛና ጥቆማ ነው ተብሏል፡፡ ተይዘዋል የተባሉት ተጠርጣሪዎች በመንግሥት ኀላፊ ነት ላይ የነበሩ ጭምር መሆናቸው የተገለጸ ሲሆን፣ በአሁኑ ጊዜ የተጠርጣሪዎችን ምርመራ በማጣራት ተጠያቂ ለማደረግ እየተሠራ መሆኑ ተመላክቷል፡፡
በሌላ በኩል በአርባ ምንጭ በጊዜያዊ ማቆያ ተጠልልው የሚገኙ ተፈናቃዮች በቂ የሚባል ሰብኣዊ ድጋፍ እያገኙ አይደለም የሚለውን ቅሬታ ኀላፊው አጣጠለውታል፡፡ ኀላፊው እንደሚሉት የክልሉ መንግሥት የተፈናቀሉ ዜጎችን በመጀመሪያ ምዕራፍ ከፌደራል መንግሥት ጋር በመተባበር አስፈላጊ የ ሰብኣዊ ድጋፍ ማቅረብና የአካባቢውን ሰላም ወደ ቀድሞው እንቅስቃሴ የመመለስ ሥር መሠራቱን ጠቁመዋል፡፡
በተጨማሪም ከአካባቢው ማኅበረሰብ ጋር በመተባበር በደረሰባቸው ጥቃት ቀያቸውን ለቀው የሸሹ ዜጎች ወደ ቀያቸው ለመመለስ ኮሚቴ ተቋቁሞ እየሠራ መሆኑን ተመላክቷል፡፡ ዜጎች ወደ ቀያቸው ከተመለሱ ብኋላ የጸጥታ ስጋት እንዳይገጥማቸው የክልሉ መንግሥት ከማኅበረሰቡ ጋር የተቀናጀ ሥራ እየሠራሁ ነው ብሏል፡፡
የግጭቱ ዋና ዋና መንስኤዎች በኮንሶ ዞን ሰገን ዙሪያ ልዩ ወረዳ የተወሰኑ ቀበሌዎችን በማደራጀት አንድ ልዩ ወረዳ እንመሠርታለን በሚል በቀጠናው የተደራጀ ቡድን የፈጸመው የኃይል እርመጃ የመጀመሪያው ሲሆን፣ ጉማይደ ልዩ ወረዳ እና አማሮ ልዩ ወረዳ የሚል ጥያቄ ያነገቡ ኃይሎች ናቸው ተብሏል፡፡ የልዩ ወረዳ ጥያቄ አቅራቢ የተባለው የተደራጀ ኃይል ሰው ከመግደል እስከ እሬሳ ማቃጠል ወንጀል ፈጽማል ተብሏል፡፡
ኹለተኛው በአሌ እና በኮንሶ ብሔረሰብ መካከል ልዩነት በመፍጠር አንድ ከተማ አስተዳደር እንመሰርታለን በማለት በኃይል የተደራጁ ኃይሎች በንጹሀን ዜጎች ላይ ግፍ እንዲፈጸም በማድረጋቸው መሆኑን ኀላፊው ለአዲስ ማለዳ አረጋግጠዋል፡፡
ቅጽ 2 ቁጥር 110 ታህሳስ 3 2013


