ትናንት አረብ ረፋድ የጠቅላይ ዐቃቤ ሕግና የኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን መሥሪያ ቤቶችን በድንገት የጎበኙት ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ አህመድ (ዶ/ር) ድንገተኛ ጉብኝት ማድረጋቸውን እንደሚቀጥሉበት አስታወቁ።
በኹለቱ የፌደራል መስሪያ ቤቶች ድንገተኛ ጉብኝትን ያደረጉት የጠቅላይ ሚንስትሩ ዓላማም በኹለቱ ተቋማት ላይ የመሥሪያ ቦታን በማስተካከል ውጤታማነትንና አፈፃፀምን በማሳደግ ረገድ የተሰሩ ሥራዎች እንዳሉ ለመገምገም ነው ተብሏል።
ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) በቀጣም ይህን መሰሉን ተግባር እንደሚያስቀጥሉ የተገለጸ ሲሆን፣ ተቋማት በእቅዳችው መሰረት ሥራቸውን በአስፈላጊው ፍጥነትና ጥራት እያከናወኑ ስለመሆኑ ለመታዘብና አቅጣጫም ለመስጠት እንዲያስችላቸው መሆኑን የጠቅላይ ሚንስትር ጽሕፈት ቤት እወቁልኝ ብሏል።
ኢትዮጵየ ለረጅም ጊዜ ግጭት ውስጥ መቆየቷን የጠቀሱት ጠቅላይ ሚንስትሩ፣ አሁን ላይ የመንግሥት ዕይታ ተስተካክሎ የምጣኔ ሃብት ልማት ላይ በትኩረት የሚሰራበት ነውም ብለዋል።
ቅጽ 1 ቁጥር 8 ታኅሣሥ 27 ቀን 2011