የደምቢ ዶሎ ዩኒቨርስቲ ፕሬዘዳንት ደላሳ ቡልቻ (ዶ/ር) ረቡዕ፣ ታኅሣሥ 24/2011 ማንነታቸዉ ባልታወቁ ግለሰቦች መታታቸው ተሰምቷል።
መረጃዎች እንደሚያመለክቱት ደላሳ ቡልቻ (ዶ/ር) ከደምቢ ዶሎ ወደ አዲስ አበባ በመጓዝ ላይ ሳሉ ነበር ቄሌም ወለጋ ዞን ሃዋ ገላ ወረዳ እገታው የተፈፀመቸዉ። የኦሮሚያ ክልል ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ኃላፊው አድማሱ ዳምጠው ለመገናነ ብዙኃን እንደገለፁት ፕሬዘዳንቱ የታገቱት ከነሹፌራቸው ነው።
ፕሬዘዳንቱ ከታገቱ በኋላ ወዴት እንደተወሰዱ እስካሁን ያልታወቀ ሲሆን ህ ጋዜጣ ለኅትመት እስከገባበት ትናንት ምሽ ድረስም የታወቀ ነገር የለም።
ስለ ጉዳዩ የጠጠየቀው የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ስልካቸው ላይ ተደጋጋሚ ጥሪን ቢያደርግም እንዳልሰራለት አመልክቷል።
የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽነ በበኩሉ ደላሳ ቡልቻ(ዶ/ር) በምን ሁኔታ ላይ እንዳሉ እያጣራ መሆኑን ገልፆ ታጋቹነ ለማግኘት ከሕብረተሰቡም ጋር በትብብር እየሰራ መሆኑን አክሏል። የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት እገታ ለብዙዎች መነጋጋሪያ የሆነ ሲሆን የአካባው ነዋሪዎችም ሥጋት ውስጥ እንደወደቁ እየገለጹ ነው።
ቅጽ 1 ቁጥር 8 ታኅሣሥ 27 ቀን 2011