መንግሥትና ኦነግ ችግራቸውን ኢንዲፈቱና ስምምነታቸውን ይፋ እንዲያደርጉ ኦፌኮ ጠየቀ

0
772

‹‹ኦሮሚያ አሁን ያለበት ሁኔታ ኦፌኮን ያሳስባል›› በሚል ርዕስ ታኅሣሥ 23 መግለጫን ያወጣው
የኦሮሞ ፌዴራላዊ ኮንግሬስ (ኦፌኮ) በኦዴፓና በኦነግ መካከል ያለው ውጥረት ሕዝብን ዋጋ እያስከፈለ መሆኑን አመልከቷል።
በሁለቱ ወገኖች አለመግባባት ኦሮሚያ ክልል ላይ የተለያዩ ችግሮች እየደረሱ የሰው ሕይወትም እየጠፋ ነው ያለው መግለጫው በቅርቡ በምዕራብ ጉጂ ዞን ፊንጫኣ አከባቢ የመንግሥት ኃይሎች እንደሚሆኑ በሚታመኑ አካላት በተተኮሰ ከባድ መሳሪያ የ13 ሰዎች ሕይወት መጥፋቱን ለአብነት በሚል አንስቷል።
እያጋጠሙ ያሉ ችግሮች እንዳይቀጥሉ መንግሥትና የኦሮሞ ነፃነት ግንባር አለመግባባታቸውን አስቸኳይ እንዲፈቱና ‹‹በሕዝቡ ውስጥ ተሰራጭተው የሚገኙ የመከላከያ ሠራዊት አባላትንና ታጣቂ ኃይሎችን ከሕዝቡ መሀከል እንዲስቡ አጥብቆ ይጠይቃል›› ሲልም ጠይቋል።
በመንግሥትና በኦነግ መካካል ያለው ስምምነት ለሕዝብ ይፋ እንዲሆንና እንዲተገበርም ኦፌኮ አሳስቧል።
ገዥዉ ፓርቲ የኢትዮጵያን ችግር ለብቻው እንደማይፈታ በመጥቀስም ‹‹የሚመለከታቸው ዋና ዋና አካላት ሁሉ የሚሳተፉበት ብሔራዊ የአንድነት መንግሥት እንዲቋቋም ደግመን እንጠይቃለን›› ሲልም አክሏል።

ቅጽ 1 ቁጥር 8 ታኅሣሥ 27 ቀን 2011

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here