የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ 70ኛ ዓመቱን እያከበረ ነው

0
598

አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ 70ኛ ዓመት በዓሉንና አልሙናይ ምስረታውን እያካሄደ ይገኛል።
በፕሮግራሙ የጠቅላይ ሚኒስትሩ የማኅበራዊ ዘርፍ አማካሪ ሚኒስትር ፕሮፌሰር ሂሩት ወልደማርያም እንዲሁም የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ፕሮፌሰር ጣሰው ወልደሃና ተገኝተዋል ፕሮፌሰሯ የአልሙናይ ምስረታ መካሄዱ የቀድሞ ተማሪዎች በዕውቀትና በሀብት ዩኒቨርሲቲውን እንዲያግዙ ከማድረግ ባሻገር፤ ተማሪዎቹ የት እንደሚገኙ እና ምን አስተዋጽኦ እያበረከቱ እንደሚገኙ ግብረ መልስ የሚያገኙበት ነው ብለዋል።
ፕሬዚዳንቱ ዩኒቨርሲቲው ከተመሰረተበት 1943 ዓመተ ምህረት ጀምሮ እስከዛሬ ድረስ ለሀገሪቱ እድገት መሰረት የሆኑ በርካታ ተማሪዎችን ወደስራ በማስገባት ትልቅ ሚና ተጫውቷል ብለዋል። በዚህም ከተመሰረተበት ጀምሮ እስከ 1971 ድረስ በመጀመሪያ ዲግሪ መርሃ ግብር ያስመርቅ የነበረ ሲሆን፤ ከ1971 በኋላ ሁለተኛ ዲግሪ መስጠት ጀምሯል።
በአጠቃላይ ዩኒቨርሲቲው እስካሁን ከ250 ሺሕ በላይ ተማሪዎችን አስመርቋል። በአሁኑ ወቅትም ከ28 ሺህ በላይ የድህረምረቃ ተማሪዎች፣ ከ18 ሺህ የቅድመ ምረቃ ተማሪዎች እንዲሁም ከ3 ሺህ በላይ የዶክትሬት ዲግሪ ተማሪዎችን እያስተማረ ይገኛል።


ቅጽ 2 ቁጥር 122 የካቲት 27 2013

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here