‹‹የቃቄ ወርድወት›› ቴአትር ከመድረክ ዛሬ ይወርዳል

0
598

‹‹የቃቄ ወርድወት›› ቴአትር ዛሬ ቅዳሜ፣ ጥር 4 ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በሚገኙበት በደማቅ ሥነ-ሥርዓት ለዕይታ ቀርቦ ከመድረክ ስንብት ይደረግለታል።
ቴአትሩም በተከታታይ ለሦስት ዓመታት ዘወትር ቅዳሜ በ8፡00 ሰዓት ለተመልካች ሲቀርብ የነበር ሲሆን የዕይታ እርዝማኔውም ኹለት ሰዓት ተኩል ነው። ‹‹የቃቄ ወርድወት›› በወልቂጤ ዞን አስተዳደር እና በብሔራዊ ቴአትር በጀት ተሸፍኖ ሲታይ መቆየቱ ታውቋል።
ቴአትሩም ትኩረት የሚያደርገው በደቡብ ክልል በጉራጌ ማኅበረሰብ ውስጥ ከዛሬ 150 ዓመት በፊት 1850 አካባቢ በማኅበረሰቡ ውስጥ የሴቶችን የመብት ጥያቄ በማንሳት ስትከራከር እና ስትሟገት የነበረች ቃቂ ውርዶት የተምትባል ጀግና ሴት ሕይወት ላይ ትኩረት አደርጎ የተሰራ ቴአትር ነው።
‹‹የቃቄ ወርድወት›› በደራሲ ጫንያለው ወልደጊዮርጊስ የተደረሰ ሲሆን 80 አንጋፋና ጀማሪ ተዋንያን ተሳትፈውበታል። ከተሳተፉት ተዋንያን መካከል አብራር አብዱ፣ ፋንቱ ማንዶዬ፣ ሱራፌል ተካ፣ መስከረም አበራ፣ ንጉሥ ባይሌ እና ትዕግስት ባዩ ይገኙበታል።

ቅጽ 1 ቁጥር 9 ጥር 4 ቀን 2011

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here