‹‹የሕያው ፈለግ›› መጽሐፍ ውይይት ይደረግበታል

0
525

በሽብሩ ተድላ (ፕሮፌሰር) የተፃፈውና በኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ የኢትዮጵያ አካዳሚ ፕሬስ የታተመው ‹‹የሕያው ፈለግ›› በተሰኘው የሳይንስ መጽሐፍ ዙሪያ የንባብና ውይይት መርሐ ግብር በቤተ-መዛግብትና ቤተ-መፃህፍት ኤጀንሲ አዳራሽ ነገ እሁድ፣ ጥር 5 ይካሄዳል።
ወይይቱ የተዘጋጀው በጀርመን ባሕል ማዕከል እና እናት ማስታወቂያ ሲሆን ከቀኑ 8፡00 ሰዓት አንስቶ ይካሄዳል። የውይይት መነሻ ዳሰሳ የሚያቀርቡት ዶ/ር ሰሎሞን ይርጋ እንደሚሆኑ በአዘጋጆች ተገልጿል።
በአካዳሚው ፕሬስ የታተመው የልዑል ራስ መንገሻ ስዩም “የትውልድ አደራ” መጽሐፍ ኅዳር 30/2011 ውይይት መደረጉ ይታወሳል፡፡

ቅጽ 1 ቁጥር 9 ጥር 4 ቀን 2011

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here