መከላከያ ታገተ!?

0
325

ሰሞኑን መነጋሪያ ከሆኑት ርዕሰ ጉዳዮቸ መካከል አንዱ በትግራይ ክልል ውስጥ የነበረው የመከላከያ ሠራዊት ክልሉን ለቆ መውጣት የለበትም በሚል የነበረው ክርክር ነው። ከዚህ ቀደም ኢትዮጵያና ኤርትራ ሠላም ማውረዳቸውን ተከትሎ በሁለቱ አገራት ድንበር አካባቢ ሰፍሮ የነበረው የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ወደ ሌሎች ስፍራዎች እንደሚንቀሳቀስ በጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) መገለጹ ይታወሳል። ይህም እርምጃ በቅርቡ ተግባራዊ መሆኑን ተከትሎ ‹‹እኛም የፀጥታ ስጋት አለብን፣ መከላከያ ሠራዊት ከትግራይ ሊወጣ አይገባም›› ያሉ የክልሉ ነዋሪዎች የመከላከያ ተሸከርካሪዎችን እንዳይንቀሰቀሱ ‹‹እስከማገት›› መድረሳቸው መነጋሪያ ሆኗል። ጠቅላይ ሚንስትሩ ቅዳሜ ከመምህራን ጋር በነበራቸው ውይይትም ይኸው ጥያቄ ቀርቦላቸው ነበር። የፌደራሉ መንግሥት በፌደራል ደረጃ የተዋቀረውን የመከላከያ ሠራዊት ስጋት ባለበትና በፈለገው ቦታ የማንቀሳቀሱ ሥልጣን እንዳለው በመጥቀስም ከክልሉ ጋር ውይይት እንደተደረገበትም አክለዋል። መከላከያ ከትግራይ ወጥቶ ክልሉ ወረራ እየተፈጸመበት የፌደራሉ መንግሥት ዝም ቢል እንኳን የአማራ ሚሊሻ ዝም ብሎ እንደማያይ ነበር ጠቅላይ ሚንስትሩ ለመምህራኑ እምታቸውን የገለጹት። ሰሞኑን የትግራይ ክልል ርእሰ መስተዳደድር ደብረፂዮን ገብረሚካኤል (ዶ/ር) በሰጡት መግለጫ ክልሉ የፀጥታ ስጋት እንደሌለለበትና መከላከያ መንቀሳቀስ የለበትም በሚል ግርግር የፈጠሩ ሰዎችም ትክክል እንዳልሆኑ ተናግረዋል። ለሕዝብ እንደራሴዎች ሪፖርት ያቀረበው መከላከያ ሚንስቴር መከላከያ አይታገትም ያለ ሲሆን ሠራዊቱ የቆየው ታግቶ ሳይሆን ነዋሪዎቹ ደኅንነት አልተሰማንም ቆዩልን እያሉ ጥሎ መሄድን ስላልመረጠ ነው ብሏል።

ቅጽ 1 ቁጥር 9 ጥር 4 ቀን 2011

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here