የኒያ ፋውንዴሽንና የጆይ ኦውቲዝም ማእከል መስራች ዘሚ የኑስ በኮቪድ ምክንያት ሕይወታቸው አለፈ

0
1196

ለ20 ዓመታት ያህል ከኦውቲዝም ጋር በተገናኘ ችግር ለደረሰባቸው ሕጻናትና ወላጆች ድጋፍ ሲያደርግ የነበረውን ኒያ ፋውንዴሽንና የጆይ ኦውቲዝም ማእከልን የመሰረቱት ዘሚ የኑስ በኮቪድ ቫይረስ ተጠቅተው በሚሊኒየም ኮቪድ-19 በፅኑ ህክምና ማዕከል ተኝተው ለሳምንታት ክትትል ሲደረግላቸው ነበር። እኚህ የብዙዎች እናት ከህመማቸው ማገገም ሳይችሉ ግንቦት 2/2013 ሌሊቱን ሕይወታቸው ማለፉ ተሰምቷል። አዲስ ማለዳ በእሳቸው ህልፈተ ሕይወት የተሰማትን ሀዘን እየገለፀች ለወዳጅ ዘመዶቻቸው፣ ለሚንከባከቧቸውና ለአድናቂዎቻቸው መፅናናትን ትመኛለች። 2012 ጥቅምት ላይ ከአዲስ ማለዳ ጋር የነበራቸውን ቆይታ ከዚህ በታች ባለው ሊንክ ያገኙታል።

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here