ተፈናቃዮች በብጥብጥ ምክንያት እርዳታ ሊደርሳቸው አልቻለም

0
701

የአለም ምግብ ፕሮግራም አዳማ ከሚገኘው መጋዘኑ ሱማሌ ክልል ዳዋ ዞን፣ ለሚገኙ ተረጂዎች መድረስ የነበረበት 436 ቶን የምግብ ውጤቶች በአካባቢው አለመረጋጋት ምክንያት ማድረስ አለመቻሉን ገለጸ።
የምግብ ውጤቶቹን የያዙት 10 ተሸከርካሪዎች ከአዳማ በመነሳት በነገሌ ወረዳ በኩል ቢንቀንሳቀሱም በዳዋ ዞን አጎራባች አካባቢዎች ባለው ብጥብጥ የተነሳ ወደ ተረጂዎች መድረስ አልቻሉም።
በዚህም ተሽከርካሪዎቹ የያዙትን ምግብ ሌሎች በሱማሌ ክልል ወደሚገኙ ተፈናቃዮች ወስዶ ለማራገፍ መገደዱን አሳውቋል።
ወደ 350 ሺህ የሚጠጉ ተፈናቃዮች በዳዋ ዞን ዕርዳታውን እንደሚጠብቁ ያሳወቀው ድርጅቱ፣ በአካባቢው ባለው አለመረጋጋትና ከመንገዱ መፈራረስ ጋር ተያይዞ ስራውን በአግባቡ መወጣት አለመቻሉንም ገልጿል።

ቅጽ 1 ቁጥር 9 ጥር 4 ቀን 2011

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here