የጥምቀት በዓል እና ሐርሞኒካ

0
630

የጥምቀት በዓል በክርስትና ሃይማኖት ተከታዮች በተለይም በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስትያን ምዕመናን ዘንድ ኢየሱስ ክርሰቶስ በ30 ዓመቱ በዮርዳኖስ ወንዝ በመጥምቁ ዮሐንስ እጅ የተጠመቀበትን ዕለት የሚያስታውሰው ኢጵፈኒያ በመባል የሚታወቀው ደማቅ በዓል ነው።በአገራችን ዛሬ ጥር 10 ቀን በከተራ ፣ በገጠር ወራጅ ውሃ የሚከተርበት ፣ ታቦታት ከየአብያተ ክርስቲያናቱ በዓሉ ወደሚከበርበት ቦታ በካህናትና በምዕመናን ታጅበው በዝማሬ፤ በዘፈን እና በሆታ በመሄድ በተዘጋጀላቸው ድንኳን ያድራሉ። ይህንን በዓል ለማክበር በከተሞች ሰው ሰራሽ ግድብ በመሰራትና ዉሃ በመከተር በዓሉን ያከብራሉ ።
በተያያዘም በአዲስ አበባ የጥምቀት በዓል ሲከበር ሐርሞኒካ የበዓሉ ማድመቂያ ሆኖ በየቦታው ውጣቶች ሲጫወቱት ይታያል።ወጣቶቹም ጥንድ ጥንድ በመሆን ክብ ስርተው ሲጨፍሩ ይታያል ።
ሐርሞኒካ ማለት አየር በመሳብ እና በማስወጣት አፍ ፣ ከንፈር እና ምላስን በመጠቀም የሚጫወቱት የሙዚቃ መሳሪያ ሲሆን የተጀመረውም በጥንት ቻይና ነው።የበለጠ ተሸሽሎ በ19ኛው ክፍለ ዘመን መጀመሪያ አካባቢ በአውሮፓ ለሙዚቃ አገልግሎት ውሏል። እንዲሁም የመጀመሪያው ዘመናዊ ሐርሞኒካ የተሰራው በጀርመን እንደሆነም ይታመናል ።
ብዙ ዓይነት የሐርሞኒካ አይነቶች እንዳሉ ቢታወቅም ዋንኞቹ ክሮማቲክ (Chromatic) ፣ ዲያቶኒክ (Diyatonic) እና የምስራቅ እስያ ትሪሞሎ (East Asia Tremolo) የሚባሉት ናቸው።
ክሮማቲክ ሐርሞኒካ ከፊል ድምፆችን የሚያወጣ ሲሆን ከሐርሞኒካ ዓይነቶች አንፃር ባህላዊ ይዘት ያለው መሳሪያ ነው።ተያይዞም ሆርን (Horn) የሚባል የሐርሞኒካ ዓይነት ሲኖር ይህንንም በአብዛኛው በምስራቅ እሲያ አካባቢ ያሉ ማኅበረሰቦች ይጠቀሙበታል።ባለ ዐሥር ቀዳዳ ዲያቶኒክ ውይም የትሪሞሎ ስልትን የተማረ ሰው በቀላሉ ሊጫወተው የሚችል ሲሆን ከሌሎቹ ቀላል የሚባል የሐርሞኒካ ዓይነት ነው።
ዲያቶኒክ ሐርሞኒካ 10 ቀዳዳ ያሉት ሲሆን በቀላሉ 19 ኖት ድምጽ መስጠት የሚችል ነው።እነዚህ የሐርሞኒካ ዓይነቶች ባለ አንድ key (የሙዚቃ ቁልፍ) ሲሆኑ አውታር (chord) እና ዜማ (melody) የሚባሉትን በአንድ እንዲያጫቱ ተደርገው የተሰሩ ናቸው።ይህንንም የሐርሞኒካ ዓይነት በሰሜን አሜሪካና በአውሮፓ ብሉስ ለሚባለው የሙዚቃ ስልት አዘውትረው ይጠቀሙታል።
ሦስተኛው የሐርሞኒካ ዓይነት የምስራቅ እስያ ትሪሞሎ የሚባለው ሲሆን ይህ የሐርሞኒካ ዓይነት አንድ ወይም ተመሳሳይ ይዘት ያለውን የዲያቶኒክ (diyatonic) ሐርሞኒካ ሲሆን የተለያዩ ዓይነት ተጨማሪ መሳሪያዎችን አካቶ የሚይዝ እና በይዘቱም እንደ ክሮማቲክ ትልቅ የሐርሞኒካ ዓይነት ነው።

ቅጽ 1 ቁጥር 10 ጥር 11 ቀን 2011

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here