የአርበኞች ግንቦት 7 የሙዚቃ ኮንሰርት ነገ ይካሄዳል

0
581

አርበኞች ግንቦት 7 ለአንድነትና ዴሞክራሲ ንቅናቄ “ኢትዮጽያዊነትን እናወድስ” በሚል መሪ ቃል በሚሊኒየም አዳራሽ ያዘጋጀው የሙዚቃ ኮንሰርት ነገ እሑድ ጥር 12 ከቀኑ 8 ሰዓት ጀምሮ እንደሚቀርብ ይጠበቃል።
ስለዝግጅቱ የዛሬ ሳምንት መግለጫን ሰጥቶ የነበረው አዘጋጅ ኮሚቴው ኮንሰርቱ ኢትዮጽያዊነትን ለማወደስ እና ድርጅቱን በመላው ኢትዮጵያ ለማደራጀት የሚያግዝ ገንዘብ ለማሰባሰብ በማለመም የተዘጋጀ ስለመሆኑ መናገሩ ይታወሳል።
በኮንሰርቱ ላይ ወጣትና አንጋፋ ድምጻውያን በታዋቂ የሙዚቃ ባንዶች ታጅበው እንደሚቀርቡም ተነግሯል።
ኮንሰርቱ የመግቢያ ዋጋ የተቆረጠለት ሲሆን ለመደበኛ 300፣ ለልዩ (ቪአይፒ) ደግሞ 500 ብር እንደሆነም ተገልጿል። አዘጋጅ ኮሚቴው በኮንሰርቱ ተገኝተው እዲያግዙትም አባላቱን፣ ደጋፊዎቹንና መላ ኢትዮጵያውያንን ጋብዟል።

ቅጽ 1 ቁጥር 10 ጥር 11 ቀን 2011

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here