ከ58 ሚሊዮን ብር በላይ ግምታዊ ዋጋ ያላቸው የኮንትሮባንድ ዕቃዎችን ባሳለፍነው ሳምንት መያዙን የገቢዎች ሚኒስቴር አስታወቀ

0
602

ባሳለፍነው ሳምንት ከ18/10/2013 እስከ 25/10/13 ዓ.ም ድረስ ከ 58 ሚሊዮን ብር በላይ ግምታዊ ዋጋ ያላቸው የኮንትሮባንድ እቃዎች መያዙን የገቢዎች ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡፡

እቃዎቹ ከሀገር ሊወጡ እና ወደሃገር ሊገቡ ሲሉ የተያዙ ሲሆን ከተያዙት ኮንትሮባንድ ቁሶች መካከል የውጭ ሀገራት ገንዘቦች፣ ወርቅ፣ የተለያዩ አልባሳት፣ ጫማ፣ ምግብ ነክ፣ የጦር መሳሪያዎች፣ ኤሌክትሮኒክስ፣ ኮስሞቲክስ፣ሲጋራ፣ ልባሽ ጨርቅ፣ መለዋወጫ፣ የሰው መድሀኒትና ሌሎችምእንደሚገኙበት ተገልጿል።

ከእነዚህም ጋር 19 ያህል ተሽከርካሪዎች ኮንትሮባንድ ሲያዘዋውሩ መያዛቸውም ታውቋል።

ሁሉም የጉምሩክ ቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች የኮንትሮባንድ እቃዎችን በመያዝ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንደተወጡ ያስታወቀው ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ጅግጅጋ፣ አቃቂ ቃሊቲ እና ሞያሌ ጉምሩክ ቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች ከፍተኛውን የኮንትሮባንድ እቃዎች የያዙ ቅ/ጽ/ቤቶች መሆናቸውን ገልጿል፡፡

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here