643 የኢትዮጵያ ሰላም አስከባሪዎች በደቡብ ሱዳን ላደረጉት የሰላም ማስከበር አገልግሎት የመንግስታቱ ድርጅት ሜዳሊያ ተሸለሙ

0
540

የክብር ሜዳሊያው ከተበረከተላቸው 643 ሰላም አስከባሪዎቹ ውስጥ 86ቱ ሴቶች መሆናቸውም ታውቋል

643 የኢትዮጵያ ሰላም አስከባሪዎች በደቡብ ሱዳን ላደረጉት የሰላም ማስከበር አገልግሎት የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የክብር ሜዳሊያ ሽልማት አበተከተላቸው፡፡

የኢትዮጵያ ሰላም አስከባሪዎች ወደ ደቡብ ሱዳን ከተሰማሩ ወዲህ በሰላም ማስከበር አገልግሎታቸው ግጭቶች እንዲቀንሱ፣ የሰብአዊ ድጋፍ ለድጋፍ ፈላጊዎች በፍጥነት እንዲደርስ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ማድረጋቸው ተገልጿል፡፡

ለኢትዮጵያ ሰላም አስከባሪዎች የተደረገው የእውቅና የሽልማት ስነ ስርዓት ላይ የመንግስታቱ ድርጅት የሰላም ማስከበር ተልዕኮ ከፍተኛ አመራሮችና ሌሎች ታላላቅ አካላት መገኘታቸውም ታውቋል፡፡

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here