የሰላም ሚኒስቴር ለሙዳይ በጎአድራጎት ማህበር የተለያዩ ቁሳቁሶችን ድጋፍ አደረገ

0
950

የሰላም ሚኒስቴር ለሙዳይ በጎአድራጎት ማህበር የተለያዩ ቁሳቁሶችን ድጋፍ አድርጓል፡፡

ሙዳይ በጎ አድራጎት ማህበር ጎዳና ላይ ወድቀው በልመና የተሰማሩና በሴተኛ አዳሪነት ህይወታቸውን ሲገፉ የነበሩ እናቶችን ከነልጆቻቸው ከችግር ውስጥ በማውጣት አዲስ ህይወት እንዲጀምሩ በማድረግ ላይ የሚገኝ የበጎ አድራጎት ማህበር ነው፡፡

የሰላም ሚኒስቴር ከፍተኛ አመራሮችም በሙዳይ በጎ አድራጎት ማህበር በመገኘት ለመተኛ የሚሆኑ ቁሳቁሶችና አልባሳትን ድጋፍ ማድረጋቸው ታውቋል።

ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል ከራስ በላይ ለሌሎች መኖርን በተግባር ላሳየን ለሙዳይ በጎአድራጎት ማህበር እውነተኛ እራስን የመስጠት ፍቅር ስላደረጉ ምስጋና አቅርበዋል፡፡

ህጻናቶችንና እናቶችን መደገፍ ለቤተሰብ መቃናት ትልቅ ትርጉም ያለው በመሆኑ አቅም በፈቀደ መጠን ድጋፉ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ተናግረዋል፡፡

ወ/ሮ ሙፈሪሃት አክለውም ከዚህ ማህበር የምንማረው ለመረዳዳትና ለመደጋገፍ ዋናው ነገር ፍቅር በመሆኑ ሁላችንም ባለን አቅም እነዚህን የመሰሉ መልካም አርዓያ የሆኑትን በእውቀት፣ በገንዘብና በጉልበት እንድንደግፍ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

የማህበሩ መስራች ወ/ሮ ሙዳይ ምትኩ ሚነስትር መስሪያቤቱ ላደረገላቸው ድጋፍ ምስጋና ማቅረባቸውን ከሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ያገኘነው መረጃ ያሳያል፡፡

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here