የሙስሊሙ ማህበረሰብ በ3ኛውን የአረንጓዴ አሻራ መርኃ-ግበር ተሳትፎ እንዲያደርግ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዝዳንት ተቀዳሚ ሙፍቲ ሀጂ ኡመር እድሪስ ጥሪ አቅርበዋል።
በኢትዮጵያ በሁሉም መስጂዶችና የእስልምና ተቋማት ግቢ ውስጥ ህዝበ ሙስሊሙ 3ኛውን የአረንጓዴ አሻራ መርኃ-ግበር ተሳትፎ እንዲያደርግ ተቀዳሚ ሙፍቲ ሀጂ ኡመር እድሪስ ጥሪ አቅርበዋል።
የችግኝ ተከላ መራሃ ግብሩ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ኡለማዎች በተገኙበት በእስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ግቢ ውስጥ መጀመሩን ኢቢሲ ዘግቧል።





