በሳዑዲ አረቢያ የሚገኙ ዜጎችን ወደ አገራቸው ለመመለስ በተያዘው እቅድ መሰረት በርካታ ዜጎቻችን በየቀኑ ወደ አገራቸው እየተመለሱ ይገኛሉ።
በዚህ መሰረትም በትናንትናው ዕለት 229 ሴቶችንና 136 ህጻናትን ጨምሮ በአጠቃላይ 2 ሺህ 42 ዜጎቻችን ወደ አገራቸው ገብተዋል።
ተመላሾቹ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ የውጭ ጉዳይና ሌሎች የሚመለከታቸው አካላትን ያቀፈው ኮሚቴ ተገቢው አቀባበል አድርጎላቸዋል ሲል የቃል አቀባይ ጽህፈት ቤት አስታውቋል።




