Save the Children ለትግራይ ክልል የሚደረገውን ድጋፍ የኢትዮጵያ መንግስት በትግራይ ክልል የተኩስ አቁም ውሳኔ ካሳለፈ በኃላ እንዳቆመ አስታውቋል፡፡
በኢትዮጲያ የSave the Childern ቃል አቀባይ የሆኑት ወ/ሮ ህይወት እምሻዉ ከአሀዱ 94.3 ሬድዮ በነበራቸው ቆይታ ነው ይህን ያሳወቁት ፡፡
ወ/ሮ ህይወት ከተናጠል ተኩስ አቁሙ አስቀድሞ ከጊዚያዊው መስተዳደሩ ጋር በመነጋገር የተለያዩ ድጋፎችን ሲያደርጉ እንደቆዩ እና የተናጠል የተኩስ አቁም ዉሳኔዉ በመንግስት በኩል ከተላለፈ በኃላ በጊዚያዊነት ለክልሉ የሚላኩ ድጋፎች እንደተቋጠ ተናግረዋል፡፡
ለመቋረጡ ዋነኛ ምክንያቶች ብለዉ ከጠቀሱት ውስጥ የድርጅቱ ሰራተኞች ደህንነት እና የመገናኛ ዘዴዎች መቋረጥ ዋነኞቹ እንደሆኑ ገልፀዋል፡፡
ነገር ግን አለም አቀፍ ግብረሰናይ ድርጅቶች ያለዉን የመገናኛ ዘዴ እና መንግስት ያመቻቸዉን ሁኔታ ተጠቅመዉ እርዳታዎችን እያቀረቡ በመሆኑ ድርጅታቸዉ ተቋርጦ የቆየዉን የሰብዓዊ ድጋፍ በድጋሚ ለመጀመር ከሚመለከታቸዉ የመንግስት አካላት ጋር እየተወያዩ እንደሆነ አንስተዋል፡፡


