̋መቅደላ˝ በተሠኘው መጽሐፍ ላይ ውይይት ይደረግበታል

0
650

የኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ የብላቴን ጌታ ኅሩይ ወልደሥላሴ የሥነ ጥበባት ማዕከል 45ኛውን የጥበብ ውሎ መርሐ ግብር ዛሬ ጥር 18/2011 ከ8 ሰዓት ጀምሮ ያካሂዳል፡፡

የአጼ ቴዎድሮስን 200ኛ የልደት ዓመት ምክንያት በማድረግ የንጉሰ ነገስቱን የመጨረሻ ዘመን የዓይን እማኝ ሆኖ ታሪካቸውን የተከታተለው ሄንሪ ሞርተን ስታንሊ በጻፈውና ገበየሁ ተፈሪ (ዶ/ር) በተረጎመው ˝መቅደላ˝ በተሰኘ አዲስ መጽሐፍ ላይ ውይይት ይደረጋል፡፡

በውይይቱ ላይ ተርጓሚውን ጨምሮ አሉላ ፓንክረስት (ዶ/ር) እና ፋሲል ጊዮርጊስ የውይይት መነሻ ሐሳብ የሚየቀርቡ ሲሆን በተጨማሪም በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የቋንቋና ሥነ ጽሑፍ መምህር ደረጀ ገብሬ፣ ሱራፌል ተካ ፣ እና አንዷለም አባተ ከመገዘዝ የቴአትር ፕሮዳክሽን መነባንብና ግጥሞች ያቀርባሉ፡፡

ቅጽ 1 ቁጥር 11 ጥር 18 ቀን 2011

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here