ምንጭ፡-ማዕከላዊ ስታትስቲክስ ኤጀንሲ 2011
መቀንጨር አንድ ሕጻን ተወልዶ በመጀመሪያዎቹ አንድ ሺሕ ቀናት የተመጣጠነ ምግብ ሳያገኝ ሲቀር በቁመትና በሰውነት መጠን በዕድሜው ልክ ሊኖረው ከሚገባው ቀንሶ ሲገኝ የሚመጣ ችግር መሆኑን ጥናቶች ያስረዳሉ። ጥር 9 በዩኒሴፍ እና ማዕከላዊ ስታትስቲክስ ኤጀንሲ በጋራ በወጣ ሪፖርት መሠረት ችግሩ እየቀነሰ ቢመጣም አሁንም አሳሳቢ ደረጃ ላይ እንደሆነ አመላክቷል።
ወደ 38 በመቶ የሚሆኑት ዕድሜያቸው ከአምስት ዓመት በታች የሆኑ ሕጻናት የመቀንጨር ችግር እንዳለባቸው ሪፖርቱ ያሳያል። ይህ ከሰባት ዓመታት በፊት ከነበረው አንፃር በአምስት በመቶ ያነሰ ሲሆን በሁለተኛው ዓለም ዐቀፍ የሥርዓተ ምግብ ማሻሻያ መርሃ ግብር መሠረት ወደ 26 በመቶ ዝቅ ለማድረግ ግብ ተቀምጧል።
በአሁኑ ወቅት አማራ ክልል ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው የመቀንጨር ችግር ያለባቸው ሕፃናት መኖሪያ በመሆን ቀዳሚ ሲሆን፤ ዝቅተኛው 14 በመቶ የመቀንጨር ችግር ያለባቸው ሕጻናት መገኛ በመሆን አዲስ አበባ ተመዝግባለች።
ቅጽ 1 ቁጥር 11 ጥር 18 ቀን 2011