አልፈራም!

0
582

ጥር 15/2011 በስዊዘርላንድ ዳቮስ የ2011ዱ የዓለም ምጣኔሀብት ጉባኤ ላይ የተገኙት ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) ንግግር አስቀድሞ በብዙዎቸ ዘንድ ሲጠበቀ ነበር። ሰዓቱ ደርሶም በኢትዮጵያና በጎረቤቶቿ ዙሪያ ስላለው የምጣኔሀብታዊ፣ ፖለቲካዊና ምኅበራዊ ትስስርና ለውጦች እንዲሁም ወደፊት ስለሚያልሙት የትብብር መንፍስ ንግግር አደረጉ፤ በመሐል በመሐሉም ከመድረኩ ታዳሚያንም የድጋፍ ጭብጨባን ሲያገኙ ተስተውሏል። ከንግግራቸው በኋላ ለፊት፣ ለፊት ጥያቄ የተቀመጡት ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ በጥያቄው ማጠቃለያ ላይ መንግሥታቸው የጀመራቸው የለውጥ ሒደቶች ወደ ኋላ ይመለሳሉ ብለው ይሰጉ እንደሆነ ጥያቄ ቀረበላቸው። እሳቸውም እንደማይሰጉ፣ በኅብረተሰቡ ውስጥ መሆናቸውንና ሕዝቡ ከጎናቸው እስከሆነ ድረስ ለውጥ ማምጣት እንደሚችሉ አጠር ያለ ምላሽ መስጠታቸው ይታወሳል።

በመልሳቸውም ‹‹አልፈራም›› ያሉ ሲሆን ከንግግራቸው ቅጽበት ጀምሮ በሺህዎች የሚቆጠሩ የፌስቡክ ተጠቃሚዎች ዐቢይ ይህን ምላሽ ሲሰጡ በነበረበት ኹነት የተወሰደን ፎቶግራፍ በመጠቀም እሳቸው ‹‹ኅብረተሰቡ ከጎኔ እስካለ ድረስ አልፈራም ለውጥ እናመጣለን›› ያሉበትን እና ‹‹እኛም ከጎንህ ነን›› የሚሉ ኢትዮጵያዊያንን ምልሽ የሚያመለክቱ ዓረፍተ ነገሮችን ጽፈው እየተጋሩትና ድጋፋቸውንም እየገለጹ ይገኛሉ። ይህም ከሰሞኑ በበርካቶች ዘንድ ብዙ ቅብብሎሽ ከነበራቸው የፎስ ቡከ ‹‹ልጥፎች›› (posts) አንዱ ሆኗል።

ቅጽ 1 ቁጥር 11 ጥር 18 ቀን 2011

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here