የኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ ፟አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ለአገር እድገት ያለው አስተዋፅኦ ፟ በሚል ርዕስ ሳይንሳዊ ገለጻና ውይይትሐሙስ፣ ጥር 30/2011 በ11 ሰዓት በኢትዮጵያ ቅርስ ጥናትና ጥበቃ ባለሥልጣን የመሰብሰቢያ አዳራሽ ያካሒዳል።
ሳይንሳዊ ገለጻውን የሚሰጡት ጌታቸው አሰፍ ሲሆኑ ገለጻቻም አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ለዕድገታችን፟፟ በምን መልኩ እንጠቀም? ፟ እና ለኢትዮጵያ ነባራዊ ሁኔታ በሚስማማ መልኩ እንዴት እናሳድገው? ዙሪያ እንደሚሆን ሳይንስ አካዳሚው በለጠፈው የድረ ገጽ ማስታወቂያ ላይ አስታውቋል።
አርቴፊሻል ኢንተለጀንስን በመጠቀም ለዕድገታቸው ያዋሉ የዓለማችን አገራት እየተበራከቱ መምጣታቸውን ተከትሎ ቴክኖሎጅውን ወደ ኢትዮጵያ ነባራዊ ሁኔታ ጋር ለጣጣም እና ጥቅም ላይ ለማዋል የውይይት መድረኩ መዘጋጀቱ ታውቋል። ዓለማችን በረቀቀ የኮምፒውተር ቴክኖሎጂ የታገዘ አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ በጥቅም ላይ መዋል ከጀመረ ሰነባብቷል፡፡ የሰው ልጆች ወይም እንስሳት ሊከውኗቸው የሚችሏቸውን ተግባራት በተቀላጠፈ፣ በፈጠነና በተሻለ የጥራት ደረጃ በመፈጸም አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ውጤታማ የሳይንስ ዕመርታ እንደሆነም ይወሰዳል፡፡
ቅጽ 1 ቁጥር 12 ጥር 25 ቀን 2011