ምንጭ፡-ዓለም ዐቀፍ የረኀብ ሪፖርት 2018
በጥቅምት 2011 ይፋ የሆነው የዓለም ዐቀፍ ረሃብ ሰንጠረዥ (Global Hunger Index) እንደሚያሳያው ረኀብ እና የተመጣጠነ ምግብ እጥረት መቀነስ አሳይቷል። በዓለም ዐቀፍ ደረጃ ረኀብ እና የተመጣጠነ ምግብ እጥረት እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር 29 ነጥብ 2 ሆኖ ሲመዘገብ፤ በ2018 20 ነጥብ 9 ሆኖ ተመዝገቧል።
አገራት የተመጣጠነ ምግብ እጥረት፣ የሕፃናት መቀንጨር እና የልጅ ሞት ላይ ከፍተኛ ለውጥ ማምጣታቸው እንደ ምክንያት ተገልጿል። በረኀብ እና የተመጣጠነ ምግብ እጥረት ከከፋባቸው አገራት 26ኛ ደረጃ የያዘችው ኢትዮጵያ ከእነዚሁ አገራት ተርታ ትሰለፋለች።
ይሁን እንጂ አሁንም ረኀብ በከፍተኛ ደረጃ ከከፈባቸው አገራት ተርታ ያለችው ኢትዮጵያ ከስምንት ሚሊየን በላይ ዜጎቿ አስቸኳይ ዕርዳታ እንደሚያስፈልጋቸው ሪፖርቶች ያሳያሉ። የሕፃናት መቀንጨር ወደ 38 በመቶ በሆነባት ኢትዮጵያ ከ21 ነጥብ 4 በመቶ ሰዎች የተመጣጠነ ምግብ አያገኙም።
ቅጽ 1 ቁጥር 12 ጥር 25 ቀን 2011