በድሬዳዋ የመልካም አስተዳደርና የሥራ አጥነት ጥያቄዎችን ለመመለስ ያግዛል የተባለ የ60 ቀናት ዕቅድ ተዘጋጅቶ ወደ ሥራ መገባቱ ተነገረ።
ዕቅዱ ሕዝብ ብሶቱን የሚያሰማባቸውን 17 ጉዳዮች በመለየት ምላሽ ለመስጠት መዘጋጀቱን ከንቲባው ኢብራሂም ዑስማን ገልጸዋል።
እንደኢዜአ ዘገባ አመራሩ ከፖለቲካ፣ ከሰላምና ፀጥታ እንዲሁም ከልማትና ከመልካም አስተዳደር አኳያ የተጀመረውን እንቅስቃሴ ዳር ለማድረስ መሥራት እንደሚገባውም አሳስበዋል።
የተጀመሩ ግዙፍ ፕሮጀክቶች ተጠናቀው የሕዝቡን የዓመታት ጥያቄ ምላሽ ለመስጠት ጥረት እንደሚደረግና በየሥፍራው የተገነቡ የመሸጫና የማምረቻ ቦታዎች ለወጣቶች እንደሚሰጡ ከንቲባው ተናግረዋል።
በከተማዋ በቅርቡ በተፈጠረው ግጭት የፖሊስና አድማ በታኝ አባላት ሳቀሩ ነገሩን በማራገብ ሲሳተፉ ነበር የተባለ ሲሆን፣ ይህም በፖሊስ ውስጥ መሠረታዊ ማሻሻያ እንደሚያስፈልግ ጠቋሚ ነው ተብሏል።
ቅጽ 1 ቁጥር 12 ጥር 25 ቀን 2011