ከንቲባው የሪል እስቴት አልሚዎች ፈጥነው ወደ ሕጋዊ መስመር እንዲገቡ አሳሰቡ

0
349

በአዲስ አበባ የሚገኙ የሪል እስቴት አልሚ ኩባንያዎች ወደ ሕጋዊ ምስመሩ እንዲገቡ ምክትል ከንቲባ ታከለ ዑማ አሳሰቡ።

በቦሌ፣ የካና ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተሞች ብቻ በተደረገ ፍተሻ ከ130 የሪል ስቴት አልሚ ኩባያዎች ስድስቱ ብቻ የቤት ግብር እየከፈሉ ሲሆን 21ዱ መክፈል ጀምረው ማቋረጣቸው ተረጋግጧል።

103 ሪል ስቴቶች ግን ምንም ዓይነት የቤት ገቢ ግብር ክፍያን አለመጀመራቸውን ፍተሻውን ያደረገው ግብረ ሃይል ማረጋገጡን ነው ያስረዳው።
ይህም ከአራት ሚሊዮን 433 ሺህ 468 ካሬ ሜትር ቦታ ላይ መሰብሰብ ይገባው የነበረን ግብር አሳጥቷል።

ከተፈቀደላቸው ይዞታ ውጭ አስፋፍተው የያዙ፣ የሊዝ ግብር ያልከፈሉ፣ ግንባታ ጀምረው ያቆሙ፣ ከተፈቀደላቸው አገልግሎት ውጪ መሬቱን የሚጠቀሙና ለሦስተኛ ወገን ያስተላለፉ ኩባንያዎች ስለመኖራቸው ተረጋግጧል።

ምክትል ከንቲባው ሕገ ወጥ ተግባራትን በሚፈጽሙት ላይ ዕርምጃ እንደሚወስዱ አስጠንቅቀዋል።

የሚጠበቅባቸውን የሊዝ፣ የቤት ግብርና ሌሎች ሕጋዊ ክፍያዎች እንዲፈጽሙም አሳስበዋል።

የቀድሞው ፕሬዘዳንት ሙላቱ ተሾመ (ዶ/ር) ከዓመት በፊት በተገኙበት የአንድ ሪል እስቴት መኖሪያ መንደር ምርቃ ላይ ጥሩ የሚሰሩ ያሉትን ያህል ቤት ለማግኘት ገንዘብ ከፍለው የሚጠብቁ ወገኖችን ገንዘብ ይዞ እስከመጥፋት የሚደርሱ ኩባንያዎች መኖራቸውን በመጥቀስ አስጠንቅቀው ነበር።

ቅጽ 1 ቁጥር 12 ጥር 25 ቀን 2011

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here