ፋሚሊ ወተት ‹‹አልትራ ሃይ ቴምፕሬቸር›› የተሰኘ ቴክኖሎጂን በመጠቀም ለስድስት ወራት ሳይበላሽ መቆየት የሚችለውን ተፈጥሮሯዊ የላም ወተት ማምረቱን ኣሳውቋል።
ይህ ቴክኖሎጂ አላስፈላጊ እና ወተት በቶሎ እንዲበላሽ የሚያደርጉ ባክቴሪያዎችን በማስወገድ ወተት ሳይበላሽ ለረጅም ግዜ ሙሉ ንጥረ ነገሮቹን እንደያዘ መቆየት እንዲችል የሚያድርግ ነውም ተብሎለታል።
ይህን ቴክኖሎጂ ለመጠቀም ድርጅቱ 100 ሚሊዮን ብር ማውጣቱን የፋሚሊ ወተት ስራ አስከያጅ ኃይሉ እሸቱ ገልጸዋል።
ድርጅቱ ለገበያ የሚያቀርበውን 60 በመቶ የወተት ግብዓት ከአርብቶ አደሮች ማኅበራት ሲረከብ፣ 40 በመቶ የወተት ምርትን ደግሞ ከልዩ ልዩ አርብቶ አደሮች ይሰበስባል።
ፋሚሊ ወተት ኤም ቢ በሚሰኝ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበር ተቋቁሞ የወተትና ወተት ተዋፅኦዎችን በማመረት ንግድ ሥራ ላይ የተሰማራ ድርጅት ነው። ድርጅቱ በ1999 ተቋቁሞ በ2000 ሥራ መጀመሩን መረጃዎች ያመለክታሉ።
ቅጽ 1 ቁጥር 12 ጥር 25 ቀን 2011