በኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ በድምፅ የታገዘ የኤ.ቲ.ኤም ማሽን አገልግሎት መስጠት ጀመረ

0
937

አቢሲንያ ባንክ በኢትዮጵያ የባንክ ኢንዱስትሪ ውስጥ የመጀመሪያ የሆነውን በድምፅ የታገዘ የኤ.ቲ.ኤም. ማሽን አገልግሎት መስጠት መጀመሩን አስታውቋል።
በቀን 24 ሰዓት በሳምንት 7 ቀን የሚሰጠው ይህን በድምፅ የታገዘ የኤ.ቲ.ኤም አገልግሎት ማሽን ዓይነ ሥውራን ደንበኞቹን ማዕከል ያደረገና የተለያየ የባንክ አገልግሎቶችን በቀላሉ ለማግኘት እንዲያስችል ታስቦ መጀመሩን ባንኩ ገልጿል።
ደንበኞቹም ይሄንን ደኅንነቱን የተጠበቀ የባንክ አገልግሎት ለማግኘት የኤ.ቲ.ኤም ካርዳቸውን በማስገባትና የኤ.ቲ.ኤም ማሽኑ ላይ የሚገኘውን የድምፅ ማድመጫ ቦታ ላይ የጆሮ ማዳመጫቸውን በማድረግ የተዘጋጁ መመሪያዎችንና ምርጫዎችን በመከተል ያሻቸውን የባንክ አገልግሎት ማግኘት ይችላሉ ተብሏል።
አገልግሎቱ በ4 ቋንቋዎች ማለትም በአማርኛ፣ እንግሊዘኛ፣ ኦሮሚኛና ትግርኛ ቋንቋዎች መቅረቡንም ባንኩ አስታውቋል።
ማንበብ ለማይችሉ ዓይነ ሥውራን፣ እንዲሁም በልዩ ልዩ ምክንያት የማየት አቅማቸው ለደከመ ሰዎች ከሌሎች የኤ.ቲ.ኤም ተጠቃሚዎች እኩል የተሟላ አገልግሎት በመረጡት ቋንቋ በአቢሲንያ ባንክ የኤ.ቲ.ኤም ማሽኖች ማግኘት እንደሚችሉም ተነግሯል።
የአቢሲንያ ባንክ ካርድ የሌሎች ባንኮች ካርዶች ወይም ዓለም አቀፍ ካርዶች እንደ ማስተር ካርድ፣ ቪዛ ካርድ እና ቻይና ዩኒየን ፔይ የያዘ ማንኛውም ሰው በባንኩ ኤ.ቲ.ኤም ይህን አገልግሎቱ ማግኘት እንደሚችልም ታውቋል።


ቅጽ 4 ቁጥር 157 ጥቅምት 27 2014

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here