ጃዋር መሐመድ የኢትዮጵያ ዜግነት ማግኘታቸውን አስታወቁ

Views: 5757

በታኅሳስ ወር የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግረስን መቀላቀላቸውን ያስታወቁት ጃዋር መሐመድ ረቡዕ ጥር 13/2012 ለኢሚግሬሽን፣ ዜግነትና የወሳኝ ኩነት የሚጠበቅባቸውን ቅድመ ሁኔታዎች በማሟላት የኢትዮጵያ ዜጋ መሆናቸውን ጠበቃቸው ለአዲስ ማለዳ ተናገሩ።

የጃዋር መሐመድ ጠበቃ የሆኑት ገመቹ ጉተማ፤ ጃዋር በዜግነት አዋጁ የሚጠበቅባቸውን ቅድመ ሁኔታዎች ማሟላታቸውን እና በዚህም መሰረት ለሚመለከተው አካል ማስገባታቸውን ገልፀዋል።

‹‹በሕጉ መሰረት ዜግነትን መልሶ ለማግኘት የምንጠብቀው ምንም ዓይነት መልስ የለም። አስፈላጊ ሰነዶችን ግን አስገብተናል›› ሲሉ ለአዲስ ማለዳ ተናግረዋል።

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com