10ቱ የመጠጥ ውሃ ተደራሽ የሆነባቸው ክልሎች

Views: 528

ምንጭ፡ – የውሃ መስኖ እና ኢነርጂ/ኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ (2018/19)

በ2018/2019 በጀት ዓመት በኢትዮጵያ የመጠጥ ውሃ ተደራሽነት ከቀደመው አንጻር በ4.8 በመቶ እድገት ያሳየ ሲሆን ይህም ከ71 በመቶ (74 በመቶ በገጠር እና 60 በመቶ በከተማ) ወደ 76 በመቶ (79 በመቶ በገጠር እና 66 በመቶ በከተማ) ባሳየው መሻሻል ምክንያት ነው። ይህም የሚያሳየው ከከተማ ይልቅ በገጠር የተሻለ የውሃ ተደራሽነት እንዳለ ነው።
ይህ ታድያ በዓመቱ መሻሻል ያሳይ እንጂ በታቀደው ልክ እንዳልተሳካ ነው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የውሃ፣ መስኖ እና ኢነርጂን ጠቅሶ በዘገባው ያካተተው።

በከተማ እና በገጠር ያለው የውሃ አቅርቦት ተደራሽነት በድምሩ ሲታይ ድሬዳዋ ከፍተኛውን ስትይዝ፣ አማራ ክልል እና አዲስ አበባ በኹለተኛ እና ሦስተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጠዋል። ይህንኑ በከተማ እና በገጠር ከፋፍሎ ያስቀመጠው የብሔራዊ ባንክ ሪፖርት፣ በክልል ደረጃ አማራ ክልል (88 በመቶ)፣ ጋምቤላ እና ሐረር (እያንዳንዳቸው በ70 በመቶ)፣ ትግራይ እና ኦሮሚያ (እያንዳንዳቸው በ66 በመቶ) እንዲሁም ቤኒሻንጉል (62 በመቶ) በቅደም ተከተል አስቀምጧቸዋል።

በከተማ ሲታይ ደግሞ ድሬዳዋ በቀዳሚነት (90 በመቶ) ደረጃ ላይ ስትገኝ፤ አዲስ አበባ (84 በመቶ)፣ አማራ (75 በመቶ) በመጀመሪያዎቹ ቅደም ተከተል ላይ ይገኛሉ። ደቡብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች እና ሶማሌ ክልል በ2018/19 ያለው ተደራሽነት በዘገባው አልተቀመጠም። ይሁንና ቀደም ያለው የ2017/18 ሪፖርት ግን በደቡብ ክልል ያለውን የመጠጥ ውሃ ተደራሽነት 57.6 በመቶ ነው ብሎ ሲያስቀምጥ፣ ሶማሌ ክልል በ77 በመቶ ላይ ይገኛል።

ቅጽ 2 ቁጥር 65 ጥር 23 2012

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com