የጃዋር መሀመድ ጥበቃዎች መነሳታቸውን ኦቢኤን ዘገበ

Views: 2259

በቅርቡ ኦፌኮን የተቀላቀሉት ጃዋር መሃመድ የፌደራል ፖሊስ ሲያደርግላቸው የነበረውን ጥበቃ ከ እሁድ ጥር 17/2012 ጀምሮ ማንሳቱን የኦሮሚያ ብሮድካስት ኮርፖሬሽን አስታወቀ፡፡

ኦቢኤን በምሽት ሁለት ሰአት ዜናው ላይ አንዳስነበበው መንግስት ለማንኛውም ተፎካካሪ ፓርቲ አመራርም ሆነ አባል የግል ጥበቃ ስለማያደርግ እና አሰራሩም ስለማይፈቅድ ጥበቃዎቹ እንደተነሱ ፌደረላ ፖሊስ አስታውቋል፡፡

አዲስ ማለዳም ባደረገችው ማጣራት ጃዋር ጠባቂዎቻቸው ወደ መደበኛ ስራቸው እንዲመለሱ እንዲያደርጉ የፌደራል ፖሊስ የወንጀል መከላከል ዘርፍ በፃፈው ደብዳቤ ማስታወቁን አረጋግጣለች፡፡

አዲስ ማለዳ ወደ ጃዋር መሃመድ በተደጋጋሚ የስልክ ጥሪ ብታደርግም ለግዜው አስተያየት ከመስጠት ተቆጥበዋል፡፡

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com