የዘንድሮው 12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ከግንቦት 24 አንስቶ ይሰጣል

Views: 486

የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ የዘንድሮው ሀገር አቀፍ የትምህርት ዘመን የ8ኛ እና የ12ኛ ክፍል ፈተና መስጫ የጊዜ ሰሌዳ  ይፋ አደረገ።

በዚህም መሠረት የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ከግንቦት 24 እስከ ግንቦት 27/2012  እንደሚሰጥ የገለጸ ሲሆን የ8ኛ ክፍል ክልል አቀፍ ፈተና ደግሞ ከሰኔ 01 እስከ ሰኔ 03/2012 ድረስ እንደሚሰጥ ኤጀንሲው አስታወቋል።

ከዚህ በፊት በተመሳሳይ ሰዓት ይሰጡ የነበሩ የማህበራዊና የተፈጥሮ ሳይንስ ፈተናዎች የተለያየ የማጠናቀቂያ ጊዜ የነበራቸው በመሆኑ በፈተናዎች አፈጻጸም ላይ ችግር ሲፈጠር  መቆየቱን ኤጀንሲው ጠቁሟል።

ተመሳሳይ ሰዓት ያላቸውን ፈተናዎች ኬሚስትሪ እና ኢኮኖሚክስ፤ ባዮሎጂ እና ታሪክ በተመሳሳይ ሰዓት እንዲሰጡ ለውጥ መደረጉንም ኤጀንሲው ገልጿል።

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com