በዓለም ዙሪያ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና የኢትዮጵያ ወዳጆች በታላቁ የኢትዮጵያውያን ጉዞ ወደ አገር ቤት ላይ እንዲሳተፉ በመንግስት የቀረበውን ጥሪ በመቀበል ወደ ኢትዮጵያ የሚመጡ እንግዶችን ለመቀበል መዘጋጀቱን የኢትዮጵያ ዲያስፖራ ማህበር አሳውቋል ተባለ።
የዳያስፖራው አባላት ወደ አገር ቤት ሲመጡ ከአቀባበል ጀምሮ ችግር እንዳይገጥማቸው ዝግጅት መደረጉን የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ማህበር ፕሬዚዳንት እድሪስ መሀመድ መናገራቸው ተዘግቧል።
በመሆኑም የዳያስፖራ አባላቱ በተለይም ጦርነቱ በነበረባቸው አካባቢዎች የመቆየት ፍላጎት ይኖራቸዋል መባሉም ነው የተሰማው።
የደህንነት ስጋት እንዳይኖርም ከሚመለከታቸው የፀጥታ አካላት ጋር እንደሚሠራም እንድሪስ አይይዘው ገልጸዋል ተብሏል።
የኢትዮጵያ ቱሪዝምና ሆቴል ማርኬት ፕሬዘዳንት ጌታሁን አለሙ በበኩላቸው ሀገራዊ ጥሪው የአገሪቱን ዲፕሎማሲያዊ፣ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ግንባታን ለማፋጠን የተቀመጠውን ዓላማ ማሳካት እንዲቻል ጥሪውን ተቀብለው የሚመጡ እንግዶችን ለማስተናገድ ሆቴሎች ከ10 እስከ 50 በመቶ የሚደረስ ቅናሽ አድርገዋል ማለታቸውን ማወቅ ተችሏል።
የሚመጡ እንግዶች ተሳትፎ የሚያደርጉባቸው ልዩ ልዩ ሁነቶች በተደራጀና በተናበበ መልኩ ብሔራዊ ኮሚቴው በሚሰጠው አቅጣጫ መሠረት የሚካሄድ ሲሆን፤ በተለይም ጦርነቱ በነበሩባቸው የአማራና አፋር አካባቢዎች አካባቢዎች ትኩረት እንደሚደረግ ይጠበቃል መባሉም ተዘግቧል።
ቅጽ 4 ቁጥር 163 ታኅሣሥ 9 2014


