አና ጎሜዝ የካቲት 9 አዲስ አበባ ይገባሉ

0
401

በ1997ቱ የኢትዮጵያ አገር ዐቀፍ ምርጫ የአውሮፓ ኅብረት የምርጫ ታዛቢ ቡድንን በመምራት የሚታወቁት ፖርቹጋላዊቷ አና ጎሜዝ ለሦስት ቀናት ጉብኝት ቅዳሜ የካቲት 9 ቀን 2011 አዲስ አበባ ይገባሉ።

አና ጎሜዝ በጉብኝታቸው ጠቅላይ ሚኒስተር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) ን ጨምሮ የተለያዩ የመንግሥት ባለስልጣናትን ፣ የፖለቲካ ፓርቲ አመራሮችን ፣ የሲቪክ ድርጅቶች ኃላፊዎችን እና ታዋቂ ግለሰቦችን አግኝተው አንደሚያነጋግሩ ተገልጿል።

ከመገናኛ ብዙኃን አውታሮች ጋርም ቆይታ እንደሚኖራቸው የሚጠበቁት አና በኢትዮጵያ የመጣውን ለውጥ ይቃኛሉም ተብሏል።
ቅዳሜ የካቲት 9 በሚሊኒየም አዳራሽ እንደሚካሄድ በሚጠበቀው የኢሳት ምክክርና የገቢ ማሰባሰቢያ ፕሮግራም ላይ እንደሚሳተፉም አስተባባሪዎቹ ተናግረዋል።

አና ከግንቦት 1997ቱ ምርጫ ማግስት ጀምሮ ከኢትዮጵያ መንግሥት ጋር መቃቃራቸው ይታወሳል። ምክንያታቸው ደግሞ ኢሕአዴግ መራሹ መንግሥት ምርጫውን አጭበርብሯል የሚል ነው። ፍትሐዊ ምርጫ አልተካሔደም ብለው የሚያምኑት አና ራሳቸውን እንደ አንድ ኢትዮጵያዊ በመቁጠርም ኢትዮጵያዊያን ዴሞክራሲና ነጻነትን በመሻት ሲያሰሙ የነበሩትን ጥያቄና የተቃውሞ ሰልፎች ሲደግፉ እንደነበር ይታወቃሉ። በዚህም በኢትጵያዊያን ዘንድ ‹‹ሀና ጎበዜ›› በሚል ቅጽል ስም እስከመጠራት ደርሰዋል።

ቅጽ 1 ቁጥር 13 የካቲት 2 ቀን 2011

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here