የድሬ ዳዋ ፖሊስ አዲስ ኮሚሽነር ተሾመለት

0
758

ኮማንደር ዓለሙ መግራ የድሬ ዳዋ አስተዳደር ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ሆነው ተሾሙ።

በቅርቡ ባጋጠመ ግጭትና አለመረጋጋት ነዋሪዎቿ ስጋት ውስጥ ወድቀውባት የነበረችው ድሬ ዳዋ አዲስ የፖሊስ ኮሚሽነር የተሾመላት ከነበረው አለመረጋት ጋር በተያየያዘ እንደሆነ ተገምቷል። ግጭቱን ተከትሎ ሲሰጡ ከነበሩ መግለጫዎች መካከል በድሬ ዳዋ የነበረው ኹከት እንዲስፋፋ በማድረግ በኩል የጸጥታ ኃይል አባላት ሳይቀሩ ተሳትፈዋል በሚል ትችት ሲሰነዘርባቸው እንደነበር ይታወሳል።

በወቅቱም በፀጥታ ኃይል መዋቅሩ ውስጥ ለውጥ እንደሚያስፈልግ ተነግሮ ነበር። ይህን ተከትሎም ኮሚሽነር የነበሩት ጌታቸው አስረስ ተነስተው ኮማንደር ዓለሙ ተተክተዋል።

አዲሱ ኮሚሽነር ለ26 ዓመታት በፖሊስ ሙያ መቆየታቸው ተገልጿል። በአዳማ፣ በቢሾፍቱ በሻሸመኔ እና በአዲስ አበባ ዙሪያ የኦሮሚያ ልዩ ዞን ከተማ የፖሊስ አዛዥ በመሆን ማገልገላቸውንም የድሬ ዳዋ ፖሊስ ኮሚሽን አስታውቋል። ላለፉት አምስት ወራት የሀረሪ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ፖሊስ ምክትል ኮሚሽነር ሆነው እያገለገሉም ነበር ተብሏል።

ኮሚሽነሩ ሹመታቸውን ተከትሎ በሰጡት አስተያየት ሕዝብን በባለቤትነት በማሳተፍ የሕግ የበላይነትን ለማረጋጥ እንደሚሰሩ ቃል ገብተዋል።

ቅጽ 1 ቁጥር 13 የካቲት 2 ቀን 2011

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here