በዩኒቨርሲቲዎች ከኹለተኛ መንፈቅ ጀምሮ የታሪክ ትምህርት መስጠት ሊጀመር ነው

Views: 392

በትምህርት ፍኖተ ካርታው ምክረ ሐሳብ መነሻነት የ2012 የዩኒቨርሲቲ ጀማሪ ተማሪዎች ከኹለተኛው መንፈቅ ጀምሮ የታሪክ ትምህርት ማስተማር እንደሚጀመር የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ።

ሚኒስትሯ ሂሩት ወልደማርያም  በአዲሱ የትምህርት ፍኖተ ካርታ በተዘጋጀ መድረክ ላይ ለአንደኛ ዓመት የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች የጋራ ትምህርቶች( ኮመን ኮርሶች) መስጠት አስፈላጊ መሆኑን የገለጹ ሲሆን የታሪክ ትምህርትን ጨምሮ 15 የትምህርት ዓይነቶች ተዘጋጅተዋል ብለዋል።

እስካሁን የታሪክ ማስተማሪያ ሞጁል ያልደረስን ቢሆንም ለኹለተኛ መንፈቅ ግን ትምህርቱን መሰጠት ይጀምራል ብለዋል።

 

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com