የወጣቶች ሥራ አጥነት እና ዴሞክራሲዊ መረጋጋት

0
540

ቴሬሴ አዜንግ እና ቲየሪ ዮጎ የተባሉ አጥኚዎች ለኻያ ዓመታት ያክል (ከ1983 እስከ 2002 ድረስ) 40 ታዳጊ አገራት ላይ ያተኮረ የወጣቶች ሥራ አጥነት፣ ትምህርት እና ፖለቲካዊ መረጋጋት ላይ የሚያተኩር ጥናት ሠርተው ነበር። በውጤቱም የወጣቶች ሥራ አጥነት ከፍተኛ በሆነበት አገር የፖለቲካ መረጋጋት እንደማይኖር አመላክተዋል፤ ሆኖም ይህ ሙሉ ለሙሉ ለሕዝባዊ አመፅ ላይዳርግ እንደሚችልም ጠቁመዋል፤ ‘ሥራ አጦቹ የተማሩ እስከሆኑ ድረስ’ በሚል።

እንደአጥኚዎቹ “ሥራ አጥነት ለፖለቲካዊ አለመረጋገት ምልክት እንጂ መንሥኤ አይደለም” ብለዋል። “የወጣቶች ሥራ አጥነት የፖለቲካ አመፅ እንደሚያስከትል የሚያሳዩ ማስረጃዎች አሉ፤ ሆኖም በኹለቱ (ሥራ አጥነት እና ፖለቲካዊ አመፅ) መካከል ያለው ግንኙነት ጠንካራ አይደለም።”

አዜንግ እና ዮጎ በዋነኝነት አራት ግኝቶችን በጥናታቸው ለይተዋል፦
የወጣቶች ሥራ አጥነት በታዳጊ አገራት ውስጥ ከጦርነት እና ፖለቲካዊ አመፅ ጋር ይያያዛል፤ ሆኖም የወጣቶቹ የትምህርት ደረጃቸው ሁኔታውን ሊቀንሰው ይችላል። የተማሩ ዜጎች የሚበዙባቸው አገራት የሥራ አጥነቱ ቁጥር ከፍተኛ ቢሆንም ለፖለቲካዊ አመፅ እምብዛም ተጋላጭ አይሆኑም። ያልተማሩ ሥራ አጦች ከተማሩ ሥራ አጦች ይልቅ ለፖለቲካዊ አመፅ ተጋላጭ ናቸው።

የሀብት ክፍፍል ልዩነት በፖለቲካዊ አመፆች ላይ ከፍተኛ አስተዋፅዖ አለው። ሥራ አጥ ወጣቶች በከፍተኛ ሁኔታ የሚያምፁት የሀብት መበላለጥ ባለበት ምጣኔ ሀብታዊ ስርዓት ውስጥ ነው።

በመፈንቅለ መንግሥታት ውስጥ የሥራ አጥ ወጣቶች መብዛት ሚናው አነስተኛ ቢሆንም አዎንታዊ ነው። አገዛዝ መቀየር ባይችሉም እንኳ ፀረ-መንግሥት ተቃውሞ ግን ይቀሰቅሳሉ።

የጥቅል ምርት ዕድገት፣ ያልተመጣጠነ ሀብት፣ የዋጋ ግዥበት የፖለቲካ አለመረጋጋት እና የሥራ አጥነት ያስከትላሉ። ሥራ አጥነት በራሱ ይህንን የፖለቲካ አለመረጋጋትን አይፈጥረውም።

እንደመፍትሔ
ጥናቱ ዴሞክራሲያዊ ስርዓት ለመገንባት ወይም ባለበት ለማቆየት የሚረዳ መረጋጋት ለመፍጠር ለወጣቶች የሥራ እና የትምህርት ዕድል መፍጠር ወሳኝ እንደሆነ ያመለክታል።

ቅጽ 1 ቁጥር 23 ሚያዚያ 5 ቀን 2011

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here