የእለት ዜና
መዝገብ

Category: በዴሞክራሲ ዓይን

ዕፅ፣ ዴሞክራሲ እና ደኅንነት

የኔዘርላንድ የመድብለ ፓርቲ ዴሞክራሲ ተቋም (NIMD) “Drugs, Democracy and Security” በሚል ርዕስ የተደራጁ ወንጀሎች በላቲን አሜሪካ የፖለቲካ ስርዓት ላይ የሚያሳድሩትን ተፅዕኖ የሚዳስስ ጥናታዊ መጽሐፍ እ.ኤ.አ. በ2011 አሳትሟል። በመጽሐፉ የመጀመሪያ ምዕራፍ የተዳሰሰው የተደራጁ ወንጀሎች እንዴት እንዳደጉ እና ለዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ እንቅፋት…

የራስን ዕድል በራስ መወሰን

በኢትዮጵያ ሕገ መንግሥት የአንቀጽ 39ን ያህል አወዛጋቢ አንቀጽ የለም። “የራስን ዕድል በራስ መወሰን እስከ መገንጠል”። አሁን በኢትዮጵያ የፖለቲካ ተዋስኦ ውስጥ የራስን ዕድል በራስ መወሰን የሚለውን ብዙ ሰዎች የሚረዱት የአስተዳደር ጉዳይ ሳይሆን የመገንጠል ጉዳይ አድርገው ነው። “እስከ መገንጠል” የሚለው ቃል የራስን…

የሥልጣን ክፍፍል ነገር

የፌዴራሊዝም ዋነኛ መርሕ የመንግሥት ሥልጣንን ያልተማከለ ማድረግ ነው። ይህም “የወል እና የተናጠል አመራር” (‘ሰልፍ ኤንድ ሼርድ ሩል’) በተባለ መንገድ ይፈፀማል። የጋራ አመራሩ በፌዴራል መንግሥቱ አማካይነት የሚከናወን ሲሆን፥ የተናጠል አመራሩ ደግሞ በክልል መንግሥታቱ አማካይነት የሚፈፀም ነው። የሥልጣን ክፍፍሉ እና ኢ-ማዕከላዊነት ወደታችኛው…

ቁጥጥር እና ሚዛን

የተቋማት መልሶ ማዋቀር ወይም ማሻሻያ (institutional reform) ጉዳይ ሲነሳ የሚታሰበው የመልካም አስተዳደር ጉዳይ ብቻ አይደለም። ቁጥጥር እና ሚዛን (check and balance) መፍጠርም አንዱ ዓላማ ነው። በርግጥ ተቋማዊ ቁጥጥር እና ሚዛንም የመልካም አስተዳደር ዘላቂ ዋስትና ነው። በኢትዮጵያ ነባራዊ ሁኔታ በሦስቱ የመንግሥት…

ነጻ ፕሬስ ለዴሞክራሲ

ዴሞክራሲያዊ በጥቅሉ ሦስት ቅርንጫፎች አሉት። ሕግ አውጪው፣ ሕግ ተርጓሚው እና አስፈፃሚው አካል። ሦስቱ እርስ በርስ እየተጠባበቁ እና የእርስ በርስ ቁጥጥር እያደረጉ ሕዝባዊ ቅቡልነት ያለው ስርዓት እንዲኖር ያደርጋሉ። ይሁንና አራተኛው የመንግሥት ቅርንጫፍ (‘fourth estate’) የሚባለው ደግሞ አለ – ነጻ ፕሬስ። ነጻ…

የወጣቶች ሥራ አጥነት እና ዴሞክራሲዊ መረጋጋት

ቴሬሴ አዜንግ እና ቲየሪ ዮጎ የተባሉ አጥኚዎች ለኻያ ዓመታት ያክል (ከ1983 እስከ 2002 ድረስ) 40 ታዳጊ አገራት ላይ ያተኮረ የወጣቶች ሥራ አጥነት፣ ትምህርት እና ፖለቲካዊ መረጋጋት ላይ የሚያተኩር ጥናት ሠርተው ነበር። በውጤቱም የወጣቶች ሥራ አጥነት ከፍተኛ በሆነበት አገር የፖለቲካ መረጋጋት…

የድርጅት ውስጥ ዴሞክራሲ

የኢትዮጵያ የፖለቲካ ፓርቲዎች መተባበር ከማይችሉበት እና አልፎ ተርፎም ከሚሰነጣጠቁበት ምክንያቶች አንዱ ውስጠ ዴሞክራሲ የሌላቸው መሆኑ ሳይጠቀስ አይታለፍም። በመሠረቱ በፓርቲያቸው የውስጥ አሠራር እና ባሕል ዴሞክራሲያዊ አካሔድን ያልገነቡ ፓርቲዎች የመንግሥትን ሥልጣን ቢቆጣጠሩም ዴሞክራሲ የመገንባት ችግር ይገጥማቸዋል። ከሁሉም በላይ ግን መንግሥት መገንባት የሚያስችላቸው…

ጉዞ ወደ ዴሞክራሲ

ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው ከመጡ ወዲህ ያለው አንድ ዓመት ለብዙ ዓመታት የሚበቃ ታሪክ ይዟል። በዴሞክራሲ ዓይን ብቻ ያየነው እንደሆነ የፖለቲካ እና ሲቪክ ምኅዳሩ ዴሞክራሲን ለመቀበል በሚያስችል መንገድ በር ተከፍቷል። ለምሳሌ፦ ፩) በሰብኣዊ መብቶች ጥሰት ሥሟ ጠልሽቶ የነበረችው ኢትዮጵያ…

ዴሞክራሲያዊ ስርዓትን ከጥላቻ ንግግር መታደግ

[ይህ ጽሑፍ ‘ኦፕንዴሞክራሲ’ ላይ በቼሪያን ጆርጅ ተጽፎ ለዚህ ዐምድ እንዲሥማማ ተቀነጫጭቦ የተተረጎመ ነው።] ሕዝባዊ ሉዓላዊነት የሚረጋገጠው የመቻቻል እና እርስበርስ መከባበር ዕሴት ሲኖር ነው። ነገር ግን አንዳንድ ቡድኖች አንድ አገር በየት አቅጣጫ ትሒድ የሚለው ላይ ለብቻቸው ለመወሰን ይስገበገባሉ። የነዚህ ቡድኖች የጥላቻ…

የኢሕአዴግ መዋሐድ ለዴሞክራሲ

ኢሕአዴግ እስካሁን አራት ክልሎችን እንወክላለን የሚሉ የአራት ፓርቲዎች ጥምረት ነበር። ይሁንና አሁን በመዋሐድ ሁሉን ዐቀፍ ፓርቲ ለመሆን እየሠራ ነው። በኢሕአዴግ ነባር የፖለቲካ ፍልስፍና የኢትዮጵያ ችግር የብሔር እና መደብ ድርብ ጭቆና ነው ተብሎ ስለሚታመን በብሔር መደራጀት ያልተጻፈ ሥምምነት ነበር። ይሁንና አሁን…

ዴሞግራፊ እና ዴሞክራሲ

የሕዝብ ስብጥር (ዴሞግራፊ) ለዴሞክራሲ ወሳኝ ነው። ዴሞክራሲያዊ ስርዓት ከሌሎች ስርዓቶች የሚለየው ሁሉንም የማኅበረሰብ ክፍሎች የመወከል ዕድል የሚሰጥ በመሆኑ ነው። የሕዝብ ስብጥር በዘውግ፣ በፆታ፣ በሃይማኖት፣ በአሰፋፈር እና ሌሎችም ከጊዜ ወደ ጊዜ ይቀያየራል። ይህ በአንድ ወቅት፣ በአንድ ቦታ ብዙ የነበሩ የማኅበረሰብ ክፍሎች፣…

ድኅረ ቅኝ ግዛት የዴሞክራሲ ግንባታ

በቅኝ ግዛት ሥር የነበሩ አገራት ነጻ ከወጡ በኋላ ዴሞክራሲያዊ ስርዓት መገንባት አለመቻላቸው ከቅኝ ግዛት አሉታዊ ዳፋዎች አንዱ ይሆን ወይ የሚለው ጥያቄ አወዛጋቢ ሆኖ ከርሟል። በተለይም ደግሞ የእንግሊዝ የቀድሞ ቅኝ ተገዢዎች የተሻለ ዴሞክራሲያዊ ስኬት አስመዝግበዋል መባሉ ችግሩ ከቅኝ ግዛት ላይሆን ይችላል…

ዴሞክራሲ እና የፓርቲዎች ቁጥር

ዴሞክራሲ በመሠረቱ የተለያዩ ርዕዮቶችን የሚያንፀባርቁ የተለያዩ ድርጅቶችን በአንድ ማዕቀፍ ማኖር የሚያስችል ያጨዋወት ሕግ ነው። በዴሞክራሲ ስርዓት የፓርቲዎች ቁጥር የሚገደብበት አሠራር የለም። በተለይ ባልዳበሩ ፖለቲካዎች ውስጥ ምንም እንኳን የርዕዮተ ዓለም ልዩነት ባይኖራቸው፣ የተለያየ ፓርቲዎችን መመሥረት፣ የተመሠረቱትን በመሰንጠቅ ወደ ብዙ መቀየር የተለመደ…

አሳታፊ ዴሞክራሲ

በኢትዮጵያ የዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ካልተሳኩባቸው ምክንያቶች አንዱ በፖለቲካ ስርዓቱ ውስጥ የልኂቃን ከፍተኛ ተዋናይነት እና የብዙኃን ዝቅተኛ ተሳታፊነት ነው። በሕግ ደረጃ የመደራጀት መብት ከተረጋገጠ ወዲህ በገዢው ቡድን ውስጥም ይሁን በተቃዋሚዎች ዘንድ ልኂቃን ብዙኃኑን ሳያሳትፉ በራሳቸው የመሰላቸውን እና የወደዱትን ሐሳብ ወይም ርዕዮተ…

የጎዳና ተዳዳሪነትን “በአፈሳ” ማጥፋት?

በመዲናችን አዲስ አበባ የጎዳና ተዳዳሪዎችን በግድ ማፈስ፣ ለተወሰኑ ጊዜያት በእስር ማቆየት፣ ያለፈቃዳቸው ሥልጠና መስጠት እና ሌሎችም የተለመዱ ናቸው። በተለይም ደግሞ እንደሰሞኑ የአፍሪካ ኅብረት ስብሰባ ሲኖር የጎዳና ተዳዳሪዎችን አፍሶ ለተወሰነ ጊዜ ጣቢያ ማቆየት እና ስብሰባው አልፎ፣ እንግዶቹ ወደየአገራቸው ከተሸኙ በኋላ ያለምንም…

ዴሞክራሲ ያለ ምርጫ ሊኖር ይችላል?

“Democracy is vicious cycle of elect and regret” የሚሉ ምሁራን መጥተዋል። መሪዎች ሕዝቦቻቸው መሥማት የሚፈልጉትን ብቻ ነግረዋቸው ሥልጣን ከተቆናጠጡ በኋላ ግን በሥራቸው መራጮቻቸውን መልሰው እንደሚያስቆጩ ለመናገር ነው ይህ አባባል የመጣው። የአሜሪካ የመጨረሻ ምርጫ ዶናልድ ትራምፕን ማምጣቱ ብዙዎችን ዴሞክራሲያዊ ምርጫ ምርጡን…

ዩንቨርሲቲዎች ለዴሞክራሲ፦ አዎንታዊ ኃይሎች?

‘ለንደን ስኩል ኦቭ ኢኮኖሚክስ’ በ72 አገራት ያሉ፣ 1500 አካባቢዎች የሚገኙ፣ 15000 ዩንቨርስቲዎች ላይ እ.ኤ.አ. በ2016 ባደረገው ጥናት ዩኒቨርሲቲዎች በምጣኔ ሀብታዊ ፍሬያማነትም ይሁን ዴሞክራሲያዊ እሴቶችን በማሳደግ ረገድ ቀጥተኛ አስተዋፅዖ እንዳላቸው አረጋግጧል። ከሕዝብ ብዛታቸው አንፃር ብዙ ዩንቨርስቲዎች ያሉባቸው አካባቢዎች የምጣኔ ሀብት ውጤታማነታቸው፣…

የዕርቃን ዳንስ ቤት “ዘመናዊ ባርነት”

በዴሞክራሲያዊ ስርዓቶች ውስጥ ባርነትም ይሁን “ዘመናዊ ባርነት” ተቀባይነት የላቸውም። “ዘመናዊ ባርነት” በጥቅሉ ሕገ ወጥ የሰዎች ዝውውርን፣ በተለይ ደግሞ ሕገ ወጥ የሕፃናት ዝውውር እና የወሲብ ዝውውር (‘ሴክስ ትራፊኪንግ’) ይመለከታል። በኢትዮጵያ በወሲብ ንግድ የሚተዳደሩ ሴቶች ቁጥር ከፍተኛ እንደሆነ ይነገራል። ዩኤንኤድስ እ.አ.አ. በ2016…

የሕዝብ አስተያየት መሰብሰብ (public opinion polling) ለዴሞክራሲ ይበጃል?

በማኅበራዊ ብዙኃን መገናኛዎች፣ በተለይም በፌስቡክ እና ትዊተር የመብት አራማጆች በፖለቲካዊ ክስተቶች ላይ እና ሌሎችንም የሕዝብ ፍላጎት ለመጠየቅ ‘ድምፅ መሰብሰብ’ን (polling) እንደ ስልት እየተጠቀሙበት ይገኛሉ። ይሁንና እንዲህ ዓይነቶቹ ‘ድምፅ አሰባሰብ’ ስርዓቶች ከመደበኛ ምርምር አካሔድ አንፃር ትክክለኛ ናሙና (‘ሳምፕል’) ስለማይኖራቸው ውጤታቸው ምንም…

ዴሞክራሲ ለልማት እንደ ቅድመ ሁኔታ…?

ልማት በግርድፉ ሲበየን ሰብኣዊ እና ምጣኔሀብታዊ ብልፅግናዎችን ያካትታል። የምጣኔ ሀብት ዕድገቱ መቀዛቀዝ ሁለገብ ልማትን ስለሚያቀዛቅዘው ተፅዕኖው የጎላ ነው የሚሆነው። ይህ ጉዳይ በተዘዋዋሪ የዴሞክራሲ ሒደቱን ሊያደናቅፈው ይችል ይሆን? ‘ዴሞክራሲ ለልማት አስፈላጊ ነው ወይስ አይደለም?’ የሚለው ርዕሰ ጉዳይ የምጣኔ ሀብት እና የፖለቲካ…

‘‘ዴሞክራሲ ከጠመንጃ አፈሙዝ ልትወለድ ትችላለች?’

የትጥቅ ትግል አሸናፊዎች ሁሉንም የሚወስዱበት፣ ተሸናፊዎች ሁሉንም የሚያጡበት (አሸናፊ-ተሸናፊ ግንኙነት የሚመራው) ስርዓት ለመውለድ የሚመች መንገድ ነው። ዴሞክራሲ ደግሞ በተቃራኒው የብዙኃኑን ይሁንታ ያገኘው የሚመራበት እና የኅዳጣን መብቶች የሚከበሩበት (ብዙኃኑን የአሸናፊነት ስሜት፣ በቁጥር ያነሰውን ደግሞ ቢያንስ የመከበር ስሜት እንዲሰማው የማድረግ መርሕ ላይ…

‘የሽግግር ጊዜ ፍትሕ’ ከዴሞክራሲ ጋር አብሮ ይሔዳል?

‘የሽግግር ጊዜ ፍትሕ’ በግርድፉ ሲተረጎም አንድ ግጭት ሲያስተናግድ ከነበረ ወይም አምባገነናዊ ስርዓት ወደ ሠላማዊ ወይም ዴሞክራሲያዊ ስርዓት ሽግግር በሚደረግበት ጊዜ ያለፈው ስርዓት ላደረሰው ሰብኣዊ ጉዳት የመቋጯ ፍትሕ ማቅረቢያ መንገድ ተደርጎ ነው። ይህ የሚደረግባቸው በርካታ መንገዶች መካከል በጣም ታዋቂው የሐቅ እና…

ሕግና ተግባር

ሁሉም ዜጎች፣ ማንም ይሁኑ ምን፣ ከሕግ በታች የመሆናቸው ጉዳይ – የሕግ የበላይነት ጉዳይ – ከዴሞክራሲ መርሖዎች አንዱ እና ዋነኛው ነው። ሕገ መንግሥቱ ደግሞ የሕጎች ሁሉ የበላይ መሆኑ እና ከሕገ መንግሥቱ የሚፃረሩ ሕግጋት ማውጣትና የሚጋጭ አካሔድ መከተል እንደማይቻል ሕገ መንግሥቱ በራሱ…

የኢትዮጵየ ፌዴራሊዝም እና ዴሞክራሲ

ዴሞክራሲ የሥልጣን ምንጩ ሁሉም ዜጎች የሆኑበት ፖለቲካዊ ስርዓት ነው፤ ፌዴራሊዝም ደግሞ የተለያዩ ትንንሽ አገራት በጥምረት የሚመሠርቱት የአስተዳደር ዓይነት ነው። ይሁን እንጂ ዴሞክራሲ እና ፌዴራሊዝም ባልተማከለ አስተዳደራዊ ምርጫቸው መሥመር ላይ ይገናኛሉ። የዚህ ዘመን ዴሞክራሲ ተዘዋዋሪ (‹ኢንዳይሬክት›) ዴሞክራሲ በመሆኑ፥ እንደ አቴናውያን ዘመን…

ስርዓተ ፆታ እና ዴሞክራሲ

እሸቱ ድባቡ “ተባእታይ አገዛዝ በኢትዮጵያ፤ ችግሩና የመፍትሔው መንገድ” በሚል ርዕስ በ1997 ባሳተሙት መጽሐፋቸው “የሴቶች ጥያቄ የዴሞክራሲ ጥያቄ ነው” ሲሉ ጽፈዋል። “ዴሞክራሲ ታዳጊ ነው። ልማት ዴሞክራሲያዊ መሆን አለበት፤ የስርዓተ ፆታ ጉዳይ ወይም ችግርም የልማት ጉዳይ ነው” ብለዋል። ብዙዎቹ ዴሞክራሲዎች ሲጀምሩ ሴቶችን…

የማንነት ጥያቄ እንደ ሰብኣዊ መብት

የአሜሪካ ሕገ መንግሥት በመጀመሪያ የመምረጥ እና የመመረጥ መብት የሰጠው ሀብት ንብረት ላላቸው ነጭ ወንዶች ብቻ ነበር። የማንነት ጥያቄዎች እየበረቱ እና እየጎለበቱ በሔዱ ቁጥር ሁሉም ነጭ ወንዶች የመምረጥ እና መመረጥ መብቶችን ተጎናፅፈዋል። ከዚያ በኋላ በትግል ሴቶች እና ጥቁሮችም እንዲሁ የመምረጥ እና…

ዴሞክራሲ ስለታሪክ ይገደዋል?

የአዲስ አበባ ጥያቄ የነዋሪዎቿ የአስተዳደር ጥያቄ ከመሆን አልፎ፣ አንድ ቀን እንኳን ጎብኝተዋት የማያውቁ ሰዎች ታሪክ እየጠቀሱ “የኛ ነች”፣ “የናንተ አይደለችም” እያሉ የሚሻሙበት ሆኗል። ይህ አተያይ ግን ከዴሞክራሲ አኳያ አንድ እርምጃ አያስኬድም። በዴሞክራሲያዊ መርሕ በአዲስ አበባ ጉዳይ መወሰን የሚችሉት የአዲስ አበባ…

error: Content is protected !!