የእለት ዜና
መዝገብ

Author: አዲሱ ደረሰ

የነጻነት ትግል፤ የደካሞች ዕርግማን?

የነጻነት ትግል እየተባለ ሕዝቦች እርስበርስ መጠፋፋት ከጀመሩ ቆይተዋል፡፡ ያልተሳካላቸው የመኖራቸውን ያህል ሕዝብን ለያይተው ለጉስቁልና እንዲሁም ለኃያላን መፈንጫ ያደረጉ የየዘመኑ ልኂቃን መኖራቸውን አዲሱ ደረሰ በጽሑፋቸው ያትታሉ፡፡ የፓናማ እንደአገር መመስረትን ታሪክ እያጣቀሱ የሱዳን ልኂቃንም ሆኑ የትግራዮቹ ራሳቸውን አኮስሰው ጉልበተኛ የውጭ አገራን ከሚያገዝፉበት…

የብሄራዊ አስቸኳይ ጊዜ ምላሽ አስተባባሪ የሚኒስሮች ኮሚቴ ከአማራ ክልል ከፍተኛ አመራሮች ጋር ውይይት እያደረገ ነው

የብሄራዊ አስቸኳይ ጊዜ ምላሽ አስተባባሪ የሚኒስሮች ኮሚቴ ከአማራ ክልል ከፍተኛ አመራር እና ከተባበሩት መንግስታትና ሌሎች አለም አቀፍ ሰብዓዊ ድርጅቶች ጋር በባህር ዳር ከተማ ምክክር እያደረገ ይገኛል። በአማራ እና አፋር ክልሎች ከቤት ንብረታቸው ለተፈናቀሉ ዜጎቻችን አፋጣኝ የሰብዓዊ ድጋፍ ማድረስ የፌደራል እና…

የአሜሪካውያን እቅድ፡ ኢትዮጵያን እንደ ሆንዱራስ፤ ዐቢይን እንደ ዜላያ

ዴሞክራሲያዊ ምርጫ አሜሪካውያንን መንግሥት ከመገልበጥ ሙከራ አያስቆምም አሜሪካ በበርካታ አገራት የውስጥ ጉዳይ መግባት ብቻ አይደለም በመንግሥት ግልበጣ እየተሳተፈች በብዙ አገራት መከራን እንዳመጣች ይታወቃል፡፡ በተለይ በደቡብ አሜሪካና አፍሪካ አገራት ተደጋጋሚ መፈንቅለ-መንግሥቶችን እያካሄደች በእጅ አዙር በርካታ አገራትን ትመራለች፤ አልሆን ካላትም ታወድማለች፡፡ ሠሞኑን…

ማንነትዎ፤ ‹ዲጂታል› ወይስ ‹አናሎግ›?

የቡድን እና የግል ማንነት ጽንሰ ሐሳብ በማኅበረሰብ ጥናት ዓውድ ውስጥ ተጽዕኖ ፈጣሪ ሆኖ ከመቶ ዓመታት በላይ ተሸግሯል የሚሉት አዲሱ ደረሰ፥ ጥራዝ ነጠቅ የማንነት ትንተና ያስከተለው አላልቅ ያለ የማንነት ፍለጋን በተመለከተ ጽሁፋቸው ዳስሳ ያደርጋል። የቡድን እና የግል ማንነት የማኅበረሰብንም የግለሰብንም ባህሪ…

በብሔሮች እኩልነት ሰበብ ሸዋን ማፍረስ?!

ሕወሓት መራሹ ኢሕአዴግ ለብሔር ብሔረሰቦች እኩልነት ታግያለሁ ቢልም በተግባር ያልተገለጠ ነበር የሚሉት አዲሱ ደረሰ፥ በተለይ በኦሮሞ እና በአማራ ማኅበረሰብ መካከል አለመተማማን እንዲኖር ከማድረግ ባሻገር አጋር የሚላቸውን ደግሞ ሌሎቹን ከሥልጣን ያገለለ ስርዓት አንብሮ ማለፉን ማስረጃዎችን በማጣቀስ በመጣጥፋቸው አስታውሰዋል። ድኅረ ሕወሓት፥ በተለይ…

ፌደራሊስቶች ወይንስ ትናንሽ ንጉሦች?

ፌደራሊዝምን ከመንግሥት አገልግሎት ጋር ማስተሳሰር ያቃተው አገራዊውን የተቋማትና የመንግሥት መዋቅሮችን ስርጭት በመተቸት አዲሱ ደረሰ መሬት ላይ ያለውን እውነታ ከገጠመኛቸውና የተሠሩ ጥናቶችንና ሰነዶችን በማገላበጥ ከመፍትሄ ምክረ ሐሳብ ጋር አዘጋጅተዋል። የኦሮሚያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ወደ አዲስ አበባ ሊዘዋወር እንደሆነ በቅርቡ ተሰምቷል። ፍርድ…

ሥራ አጥነትን ገንዘብ በማሳተም መቅረፍ ቢቻልስ?

በአንድ አገር ውስጥ የሚገኙ የሥራ አጦች ቁጥር ከፍተኛ እየሆነ በሄደ ቁጥር በኢኮኖሚው ላይ የሚያሳድረው ተጽእኖ ከባድ ነው፡፡የሥራ አጥነት ቁጥርን መቀነስ ለመንግሥት ትልቅ ግቡ ነው፡፡ ምክንያቱም የዜጎች ሥራ አጥ በማኅበረሰብ ውስጥ የሚያሳድረው የኢኮኖሚ እና ሞራል መላሸቅ አገርን ወደ አልተፈለገ ውጥረት ውስጥ…

ድህረ ሕውሃት የኢትዮ-ኤርትራን ዕጣ ፋንታ እንዴት ይወስናል?

የኹለተኛ ደረጃ ትምህርት መልቀቂያ ፈተና ወስደው ለውጤት በሰላም እንገናኝ ተባብለው ከተለያዩት ጓደኛሞች መሀከል ከፊሎቹ ተመልሰው አልመጡም። ምክንያቱም የኢትዮ-ኤርትራ ጦርነት በመፈጠሩ፤ በአንድ ወቅት በአንድ ክፍል ተማሪዎች በድንገት የኹለት አገር ዜጎች ሆነው ተገኝተዋል። ይህ አጋጣሚ ብዙ ሁነቶችን አስከትሏል። እናት እና አባትን ለያይቷል፤…

This site is protected by wp-copyrightpro.com