መዝገብ

Category: አቦል ዜና

ኢትዮ ቴሌኮም ዋትስአፕ፣ ቫይበር፣ ቴሌግራምና ሌሎችንም አላግድም አለ

ኢትዮ ቴሌኮም እንደ ‹ዋትሳፕ›፣ ‹ሜሴንጀር›፣ ‹ቫይበር›፣ ‹ኢሞ›፣ ‹ዊቻት› እና ‹ቴሌግራም› ያሉ የማኅበራዊ የመገናኛ መተግበሪያዎችን የመዝጋት ፍላጎት እንደሌለው ገለጸ። ኢትዮ ቴሌኮም የማኅበራዊ መገናኛ መተግበሪያዎች ላይ የክፍያ ታሪፍ ለማውጣት አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝም ለመዝጋት የሚያስችለውን የቴክኖሎጂ ግዢ ፈጽሟል የሚባለው መረጃ ውሸት እንደሆነ አስታውቋል።…

ከጫት የተገኘው የውጪ ንግድ ገቢ ከቡና በእጥፍ በለጠ

ባለፉት ሁለት ወራት በታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ ከጫት የተገኘው የውጪ ንግድ ገቢ ከቡና ከተገኘው በሁለት እጥፍ የሚበልጥ መሆኑ ታወቀ። ኢትዮጵያ በጥቅምትና ኅዳር ወራት በአገሪቷ ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ ወደ ሦስት ቢሊየን ብር የሚያወጣ ጫት የላከች ሲሆን ከቡና የተገኘው ደግሞ ወደ አንድ ነጥብ…

ሜቴክ 6 ቢሊየን ብር ቀረጥና ታክስ እንዲከፍል ተጠየቀ

በተለምዶ ሜቴክ ተብሎ የሚጠራው የብረታ ብረት ኢንጅነሪነግ ኮርፖሬሽን (ብኢኮ) ስድስት ቢሊየን ብር ወዝፍ ቀረጥና ታክስ እንዲከፍል በገቢዎች ሚኒስቴር መጠየቁን አዲስ ማለዳ ከተለያዩ ምንጮች አረጋገጠች። ኮርፖሬሽኑ ለባለፉት ዓመታት በአራት የጉምሩክ ጽሕፈት ቤቶች በተለያዩ ጊዜያት ላስገባቸው ቁሳቁሶች የሚጠበቅበትን ቀረጥና ታክስ በሚገባ አለመክፈሉ…

የመጀመሪያው የሕክምና ዕቃዎች ማስወገጃ ሥፍራ በ2 ወር ሥራ ይጀምራል

የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅርቦት ኤጀንሲ መቶ ሚሊየን ብር የሚያወጣና ለአገሪቷ የመጀመሪያ የሆነ የተበላሹና ከአገልግሎት ውጪ የሆኑ መድኃኒትና ያገለገሉ የሕክምና ዕቃዎች ማስወገጃ ሥፍራ በአዳማ ገንብቶ ለማጠናቀቅ መቃረቡ ተገለጸ። የማሽን ተከላና የቢሮ ግንባታ መጠናቀቁን የገለጹት የኤጀንሲው የኮሚኒኬሽን ኃላፊ አድና በሬ በዓይነቱ ልዩና በመጠንም…

9 ዓመት የዘገየው ሕንፃ ከ295 ሚሊየን ብር በላይ ተጨማሪ ወጪ አስወጣ

ኢባትሎአድ በሚል የግንባታ ፕሮጀክት ሥም እየተገነባ ያለው የኢትዮጵያ የባሕር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ አገልግሎት ድርጅት ዋና መሥሪያ ቤት ሕንፃ ግንባታው በወቅቱ ባለመጠናቀቁ ከ295 ሚሊየን ብር በላይ ተጨማሪ ወጪ አስወጣ። በሦስት ዓመት መጠናቀቅ የነበረበት ሕንፃው ለተጨማሪ ዘጠኝ ዓመታት ዘግይቶም ባለመጠናቀቁ በድጋሚ ለስድስት ወራት…

የቤንዚን ኮንትሮባንድ የነዳጅ እጥረት አስከተለ

በያዝነው ዓመት በአገሪቷ የገባው የቤንዚን መጠን ካለፈው ዓመት ጋር ሲነጻጸር በ15 በመቶ ቢያድግም ከፍተኛ እጥረት አጋጥሟል። ለዚህም የቤንዚን ጥቁር ገበያ መስፋፋትና የኮንትሮባንድ ንግድ መጠናከር እንደ ዋና ምክንያት ቀርቧል። እጥረቱ በዚህ በያዝነው ኅዳር ወር ሲያጋጥም ለሁለተኛ ጊዜ ሲሆን በአዲስ አበባና በሌሎች…

ኤች ሲ በአማካይ 750 ሺሕ ቶን የድንጋይ ከሰል ለማቅረብ ተስማማ

የኢትዮጵያ ነዳጅ አቅርቦት ኢንተርፕራይዝ ለድንጋይ ከሰል አቅራቢዎች አውጥቶት በነበረው ጨረታ ላይ ኤች ሲ ትሬዲንግ ኃ/የተ/የግ/ማኅበር አሸነፈ። በመሆኑም ከደርባን ሲሚንቶ ፋብሪካ ውጪ ላሉት የሲሚንቶ ፋብሪካዎች 2 ነጥብ 2 ቢሊዮን ብር የሚገመት፣ በዓመት በአማካይ 750 ሺሕ ቶን የድንጋይ ከሰል ለማቅረብ ተስማምቷል። ጨረታው…

በሐዋሳ ደረቅ ወደብ ሊገነባ ነው

በሐዋሳ በተከራየው መሬት ላይ የደረቅ ወደብ አገልግሎት እየሰጠ የሚገኘው የኢትዮጵያ የባህር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ አገልግሎት ድርጅት ለወደብ ግንባታ የሚሆን ሦስት ሄክታር መሬት ተረከበ። የድርጅቱ የሕዝብ ግንኙነት ቡድን መሪው አሸብር ኖታ ድርጅቱ እስከ አሁን ድረስ በሐዋሳ በተከራየው መሬት ላይ የደረቅ ወደብ አገልግሎት…

የፈረሱ ተቋማት ሠራተኞች አለመመደብ ቅሬታ አስነሳ

በአዲሱ የአስፈጻሚ ተቋማት አደረጃጀት በፈረሱ ተቋማት ውስጥ ከነበሩ ሠራተኞች መካከል እስካሁን ያልተመደቡ መኖራቸው ቅሬታ አስነሳ። የሠራተኞች ምደባ እስከመቼ ይጠናቀቃል ለሚለው የተቆረጠ ጊዜ ማስቀመጥ እንደማይቻል ሲቪል ሰርቪሰ ኮሚሽን ገልጿል። ከፈረሱት ተቋማት መካከል ከ180 እስከ 200 ሠራተኞች ያሉት የሆርቲካልቸርና ግብርና ኢንቨስትመንት ባለሥልጣን…

ኤሌክትሪክ ኃይል ሩብ ትሪሊየን ብር ዕዳውን መክፈል አቅቶታል

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል 216 ቢሊየን ብር ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በኮርፖሬት ቦንድ መልኩ መበደሩንና መክፈል የሚችልበት አቋም ላይ እንደማይገኝ አዲስ ማለዳ ከተለያዩ ምንጮች አረጋገጠች። ድርጅቱ ከውጭ አበዳሪዎች ከወሰደው ብድር ጋር ሲደመር ቁጥሩ ከሩብ ትሪሊዮን ብር ሲያልፍ የአገሪቱን 75 በመቶ በጀት ያክላል።…

በሳምንት ዘጠኝ ሺሕ አህዮች በኮንትሮባንድ ወደ ኬንያ ለእርድ ይላካሉ

‹ዶንኪ ሳንክቿሪ› የተባለ አገር በቀል ድርጅት ባደረገው ጥናት በሳምንት ከ9000 በላይ አህዮች ከኢትዮጵያ እየወጡ ኬኒያ ለሚገኙ ቄራዎች በሕገወጥ መንገድ እንደሚቀርቡ ገለጸ። በተለይም ‹ስታር ብርሊየት› የተባለ የቻይና ድርጅት አህዮቹን ያቤሎ ከተማ ውስጥ በሚገኘው የኪናማ ገበያ እንደሚገዛ ባለፈው አንድ ወር የተደረገውን ጥናት…

“ከአገር ዐቀፍ ፓርቲዎች ሕጋዊዎቹ ሰባቱ ብቻ ናቸው”

በአሁኑ ወቅት በአገር ዐቀፍ ደረጃ ከተመዘገቡት 22 የፖለቲካ ፓርቲዎች ውስጥ የፖለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባ አዋጅ የሚያስቀምጣቸውን ግዴታዎች አሟልተው የሚገኙት ሰባት ብቻ መሆናቸው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ገለጸ። የተቀሩት ፓርቲዎች ሕጉ ከዓመታዊ የሥራ እና የሒሳብ አያያዝ እንዲሁም ከሌሎች ቅድመ ሁኔታዎች ጋር በተየያዘ…

ተጠርጣሪዎችን በማሸሽ የተጠረጠሩት ታሰሩ

ከሥራ ቀን ውጪ ጸሐፊያቸውን በማዘዝ በሙስና ወንጀል የተጠረጠሩትን ሜጀር ጀኔራል ሐድጉን ሰነድ አሽሽተዋል በሚል የተጠረጠሩት የሜቴክ የሰው ሀብት ክፍል ኃላፊ የሆኑት ኮሎኔል ሰጠኝ ካሣዬ ኅዳር 10 ቀን ፍርድ ቤት ቀርበው፣ በመንግሥት ተከላካይ ጠበቃ እንዲቆምላቸው የተወሰነ ሲሆን ኅዳር 13 በዋለው ችሎት…

ኢንቨስትመንት ባንክ ሴቶችን ለማበረታት አንድ ቢሊየን ብር የሚጠጋ ብድር ፈቀደ

የአውሮፓ ኢንቨስትመንት ባንክ ወደ አንድ ቢሊየን ብር የሚጠጋ፣ በረጅም ጊዜ የሚከፈል ብድር ሴቶች በኢኮኖሚ ላይ ያላቸው ተሳትፎ ለመጨመር ለኢትዮጵያ ለመስጠት ወሰነ። ብድሩ መንግሥት ሴቶች በኢኮኖሚው ጉልህ አስተዋጽኦ እንዲያበረክቱ የተለያየ ተግባራትን እያከናወነ በሚገኝበት ወቅት መሆኑ ሚናውን ከፍ ያደርገዋል ተብሏል። የባንኩን ወሳኔውን…

በ2012 ሰማንያ በመቶ የሞባይል ካርድ ሽያጭ ይቆማል

ዕቅዱ ሲሳካ ወደ ሁለት ቢሊዮን ብር ያህል ወጪ ማስቀረት ይቻላል ኢትዮ ቴሌኮም በሚቀጥለው ዓመት መጨረሻ የሞባይል ካርድ ሽያጭን ሰማንያ በመቶ እንደሚያስቀር ለአዲስ ማለዳ አስታወቀ። በያዝነው ዓመት መጨረሻ ደግሞ ሃምሳ በመቶ የሚሆነው የሞባይል ካርድ ሽያጭ ይቀራል። የሞባይል ካርድ ሽያጭ በከፍተኛ ደረጃ…

ያሬድ ዘሪሁን ሹመት ይሰጠኛል ብለው እየጠበቁ ነበር

ፖሊስ በያሬድ ዘሪሁን ላይ የሚያካሒደውን ምርመራ አጠናቅሮ በ14 ቀናት ውስጥ እንዲያቀርብ የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 10ኛ የወንጀል ችሎት ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጠ። የቀድሞው የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት ምክትል ዳይሬክተር እና የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ጄነራል የነበሩት ያሬድ ዘሪሁን በሰብኣዊ…

ዐቃቤ ሕግን ያስፈራሩት ግለሰብ ፍርድ ቤት ቀረቡ

በሜቴክ የሥራ ኃላፊዎች የተፈፀመ የሙስና ወንጀልን የሚያጣሩ ዐቃቤ ሕጎች ጋር በመደወል ምርመራውን እንዲያቋርጡ ዛቻ እና ማስፈራሪያ በማድረስ እና የዐቃቤ ሕግ ሥራን በማደናቀፍ ተግባር ተጠርጥረው የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 10ኛ የወንጀል ችሎት የቀረቡት የኮሎኔል ጉደታ ኦላና ምርመራ ተጠናቆ እንዲቀርብ…

በዩኒቨርሲቲዎች የግጭቶች ስጋት አንዣቧል

በአሶሳ ዩኒቨርሲቲ ግጭት 3 ተማሪዎች ሞተዋል 31 ቆስለዋል የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች እያጋጠሙ ያሉ ግጭቶች ሰለባ እንዳይሆኑና ትምህርታቸውን ተረጋግተው ትምህርታቸውን እንዲከታተሉ መንግሥት ጠየቀ። ሰሞኑን በአሶሳ ዩኒቨርሲቲ በተከሰተ ግጭት የሦስት ተማሪዎች ሕይወት ማለፉን ተከትሎ ግጭቶች ወደ ሌሎች ዩኒቨርሲቲዎች እንዳይዛመቱ ተማሪዎች ተረጋግተው መማር እዳለባቸው…

የብርቱካን ሚዴቅሳ ሹመት ቀጣይነት አጠራጣሪ ሊሆን ይችላል

የሕግና ፍትሕ ጉዳዮች አማካሪ ጉባኤ የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አዋጅ ሲሻሻል የቦርዱ አባላት አባል ከመሆናቸው በፊት ምንም ዓይነት የፖለቲካ ተሳትፎ ያላደረጉ መሆን እንደሚገባቸው የሚያደነግግ አማራጭ ሐሳብ አቀረበ። ጉባኤው በፌዴራል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ሥር 13 የሕግ ምሁራን እና የህግ ባለሙያዎች ስብስብ የተዋቀረ…

በአዲስ አበባ ከታሰሩት እስካሁን ያልተፈቱ አሉ

የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) ወደ አገር መመለሱን ተከትሎ መስከረም 5/2011 ከተደረገው የአቀባበል ሥነ ስርዓት ጋር ተያይዞ በአዲስ አበባ እና ዙሪያዋ በተነሳው ሁከት ፖሊስ በቁጥጥር ሥር ያዋላቸው ነገር ግን እስከ አሁን ድረስ ያልተፈቱ ግለሰቦች ይገኛሉ ተባለ። በኦነግ አቀባበል ወቅት በተቀሰቀሰ ሁከት…

የፀረ ጥላቻ ንግግር ሕግ ሊወጣ ነው

የፌደራል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ እስከ ሁለት ዓመት የሚያከናውናቸውን ዕቅዶች በተመለከተ በሰጠው መግለጫ “የፀረ ጥላቻ ንግግር ሕግ” በዚህ ዓመት ሊያወጣ እንደሆነ ገለጸ። ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ በመሻሻል ላይ ካሉ እና አዲስ ከሚዘጋጁ የሕግ ማዕቀፎች መካከል በማኅበራዊ የመገናኛ ብዙኃን አውታሮች እና በሌሎችም ስልቶች…

የመድኃኒት አቅርቦት ኤጀንሲ 353 ሚሊየን ብር ማባከኑ ታወቀ

የመድኃኒት አቅርቦት ኤጀንሲ በአገሪቷ 17 መጋዘኖች፣ መድኃኒት ማከማቻና ቢሮዎች ግንባታዎች ባካሔደበት ወቅት ያልተገባ 353 ሚሊየን ብር ማውጣቱ ታወቀ። አዲስ ማለዳ ከፌዴራል ኦዲተር ዋና መሥሪያ ቤት ያገኘችው መረጃ እንደሚያመለክተው ኤጀንሲው የመድኃኒት ማከማቻ መጋዘኖችና ቢሮዎች ለማስገንባት ከአራት ሥራ ተቋራጮች ጋር በ152 ሚሊየን…

ማዕከላዊ ሙሉ ለሙሉ አልተዘጋም

ዮርዳኖስ ሆቴል ላይ ለሚገኘው ቢሮው፥ ኮሚሽኑ በወር ሁለት ሚሊዮን ብር ይከፍላል ከ40 ለሚበልጡ ዓመታት የሰቆቃ ማዕከል ሆኖ የቆየው ማዕከላዊ እስር ቤት ሙሉ ለሙሉ እንዳልተዘጋና በከፊል ለቢሮ አገልግሎት እየዋለ እንደሚገኝ አዲስ ማለዳ ፌዴራል ፖሊስ ከሚገኙ የተለያዩ ምንጮች አረጋገጠች። በፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን…

የግል አልሚዎችን በቤቶች ግንባታ ላይ ለማሳተፍ መንግሥት ምክረ ሐሳብ አቀረበ

የውጭ እና የአገር ውስጥ ባለሃብቶችን በጋራ መኖሪያ ግንባታዎች ለማሳተፍ በከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ሚኒስቴር ምክረ ሐሳብ ቀርበ። ከ20 የማይበልጡ የግል አልሚዎች በተሳተፉበት በሲቪል ሰርቪስ ዩንቨርስቲ በተደረገ የምክክር መድረክ በቀረበው ሰነድ በቤት ግንባታው የሚሳተፉ ባለሀብቶች መነሻ ካፒታል 50 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር እንዲሆን…

ኃይሌ ሪዞርት ባሳለፍነው በጀት ዓመት 150 ሚሊዮን ብር ገቢ አገኘ

እ.አ.አ በ2025 የሆቴሎቹን ቁጥር ሃያ ለማድረስ አቅዷል በጅቡቲ፣ ሶማሊያና ኤርትራ መዋዕለ ንዋይ ለማፍሰስ አቅዶ እየሠራ ነው ኃይሌ ሪዞርት በአራት ሆቴሎች ለመሰብሰብ አቅዶ ከነበረው 167 ሚሊዮን ብር ገቢ 150 ሚሊዮን ብር ማግኘቱ ታወቀ። ሆቴሎቹ በዕቅድ ከተቀመጠላቸው ገቢ አንጻር 89 በመቶውን ቢያሳኩም…

በስህተት ተፈትተው የታሰሩት ባለሀብት ጉዳያቸው በድጋሚ ይታያል

በአራጣ ማበደር፣ በታክስ ማጭበርበር፣ በሀሰት ማስረጃና በሕገ ወጥ ገንዘብ ዝውውር 25 ዓመት ተፈርዶባቸው በእስር ላይ የነበሩት ከበደ ተሰራ የፌደራል ታክስ አስተዳደር አዋጅ በመሻሻሉ እና የሕገ መንግሥቱ አንቀፅ 22(2) በሚደነግገው መሰረት በአዲሱ አዋጅ መሰረት የእስር ቅጣቴ ሊቀንስልኝ ይገባል በሚል ለፌደራል ከፍተኛ…

በሞያሌ ግጭት አገርሽቷል

በግጭቱ 19 ሰዎች መሞታቸው ተገለጸ በሞያሌ ከተማ በተቀሰቀሰ ግጭት የ19 ሰዎች ሕይወት ማለፉ ተገለፀ። ግጭቱ በመሬት ይገባኛል ቅራኔ መነሳቱ የታወቀ ሲሆን፤ የሠላም ሚንስቴር የሟቾች ቁጥር አለመታወቁን ጠቅሶ የፌደራል ጸጥታ ኃይል ጣልቃ መግባቱን አሳውቋል። የኦጋዴን ብሔራዊ ነፃነት ግንባር (ኦብነግ) ባወጣው መግለጫ…

ባለፉት አራት ወራት 544 ሰዎች ምሕረት አግኝተዋል

አርበኞች ግንቦት ሰባትና ኦነግ ስለምሕረት አዋጁ አፈፃፀም የሚያውቁት ነገር እንደሌለ ገልፀዋል ለስድስት ወራት እንዲቆይ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ባጸደቀው የምሕረት አዋጅ ያለፉት አራት ወራት 544 ግለሰቦች የምሕረቱ ተጠቃሚ መሆናቸውን የፌዴራል ጠቅላይ አቃቤ ሕግ አስታወቀ፡፡ የምህረት አዋጁ የሚመለከታቸው ግለሰቦች በቀሪው ጊዜ…

ከታቀደው 11 ቢሊየን ብር በላይ ያስወጣው የመስኖ ግድብ ተጨማሪ በጀት ጠየቀ

የግድቡ ስፋት የጣናን ሃይቅ አንድ ዐሥረኛ ያክላል በሳምሶን ብርሃኔ ለአራት ዓመታት አካባቢ የዘገየውና መንግስትን ከ11 ቢሊየን ብር በላይ ተጨማሪ ወጪ ያስወጣው በወልቃይት ወረዳ የሚገኘው የዛሬማ ሜይዴይ የመስኖ ግድብ ለማጠናቀቅ ተጨማሪ አንድ ቢሊየን ብር በጀት እንደሚያስፈልግ ተገለፀ። በአፍሪካ ውስጥ ከሚገኙት ትላልቅ…

የበጎ አድራጎት ድርጅቶችና ማኅበራት አዋጅ ማሻሻያ ውዝግብ አስነሳ

በማሻሻያው የበጎ አድራጎት ድርጅቶችና ማኅበራት ኤጀንሲ ቅሬታ እንደተሰማው ገለጸ ረቂቅ ሕጉ ከነአጨቃጫቂነቱ ወደ ሚኒስትሮች ምክር ቤት ተመርቷል የበጎ አድራጎት ድርጅቶችና ማሕበራት አዋጅ ማሻሻያ ላይ እንዳልሳተፍ ተደርጌያለሁ ሲል የበጎ አድራጎት ድርጅቶችና ማሕበራት ኤጀንሲ መንግሥትን ወቀሰ። መንግሥት ግን የሕግ ማዕቀፍ ማሻሻያው መደረግ ያለበት…

This site is protected by wp-copyrightpro.com