መዝገብ

Category: አቦል ዜና

የዐሥር ዓመቱ የልማት ዕቅድ ጅማሮ

በቅርቡ በሚኒስትሮች ምክር ቤት የፀደቀውን የዐሥር ዓመት የልማት እቅድ ላይ የፕላን ኮሚሽን ከሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ለሁለት ቀናት የሚቆይ ውይይት አካሂዷል። በሳምንቱ መጀመሪያ የሥራ ቀናት በተካሄደውን የውይይት መድረክ፤ፍፁም አሰፋ(ዶ/ር) የኮሚሽኑን ያለፉ አፈፃፀሞችና ተግዳሮቶች፣ የአገር በቀል ኢኮኖሚያዊ ማሻሻያዎችና የዐሥር ዓመት…

በአዲስ አበባ የወርቅ ማቅለጫ ሊገነባ ነው

በአዲስ አበባ ከተማ አለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ የወርቅ ማቅለጫ እንደሚገነባ የማአድንና ነዳጅ ሚኒስቴር አስታወቀ። ይህንን የወርቅ ማቅለጫ መገንባት እንደ ኢትዮጵያ ላለች የወርቅ ማዕድን ላላት አገር ጠቀሜታው የጎላ እንደሆነ የማአድንና ነዳጅ ሚኒስትር ኢንጂነር ታከለ ኡማ ተናግረዋል። ሚድሮክ እና ሌሎች የተለያዩ ኩባንያዎች…

አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለተፈናቃዮች የላከው ድጋፍ አልደረሰም ተባለ

አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል በጸጥታ ችግር ምክኒያት ለተፈናቀሉ ዜጎች የላከው ሦስት ሺሕ ኩንታል የምግብ ድጋፍ ለተፈናቃዮች አለመድረሱ ተገለጸ። የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል ስምንት ነጥብ ስድስት ሚሊየን ብር የሚገመት የምግብ እህል ድጋፍ ማድረጉ የሚታወስ ሲሆን፣…

“በጸጥታ ችግር ከተጎዱ ኢንቨስትመንቶች ማገገም የሚችሉት አንድ በመቶ ያክሉ ናቸው” የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ኮሚሽነር ሌሊሴ ነሚ

ኢትዮጵያ ውስጥ በጸጥታ ችግር ሰላባ ሆነው ከሚወድሙ የኢንቨስትመንት ልማቶች ውስጥ ከደረሰባቸው ጉዳት አገግመው ወደ ሥራ የሚመለሱት ከአንድ በመቶ በላይ እንደማይሆኑ የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ኮሚሽነር ሌሊሴ ነሚ አስታወቁ። ኢትዮጵያ ውስጥ ከ2008 እስከ 2013 ከ400 በላይ የኢንቨስትመንት ልማቶች መውደማቸውን ኮሚሽነሯ ተናግረዋል። ቁጥሩ…

በምሥራቅ ወለጋ ዜጎች መንግሥት ከለላ እያደረገልን አይደለም አሉ

በኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ወለጋ ውስጥ በሚገኑት በሆሮ ጉድሩ ወላጋ፣ ሊመ ገሊላና ኪረሙ ወረዳ የሚኖሩ ዜጎች መንግሥት ደህንነታችንን ከማስጠበቅ ይልቅ ለሚደርስብን ችግር ተባባሪ ሆኖብናል ሲሉ ቅሬታቸውን ገለጹ። በምስራቅ ወለጋ በተደጋጋሚ በሚደርሱ የጸጥታ ችግሮች እየተንገላታን ነው የሚሉት የአካባቢው ኗሪዎች በተደጋጋሚ ችግር የማያጣቸው…

ኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ የንግድ ፖሊሲ እያዘጋጀች ነው

በኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ የንግድ ፖሊሲ እየተዘጋጀ መሆኑን የንግድ እና ኢንዱስትሪ ሚንስትር ዴኤታ እሸቴ አስፋው ለአዲስ ማለዳ አስታወቁ። ይህ የንግድ ፖሊሲ ከሁሉም የዓለማችን አገራት ጋር ተወዳዳሪ ሊያደርገን የሚችል ሲሆን በእኛ አገር ሕጎች ሁሉ የሚቀዱት ከፖሊሲ በመሆኑ የንግድ ፖሊሲ የግድ መኖር አለበት።…

የእነ ዳውድ ኢብሳ ቡድን ምርጫ ቦርድን ዋሽቶኛል ሲል ከሰሰ

የእነ ዳውድ ኢብሳ ቡድን የሆነው የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) ምርጫ ቦርድ እንደዋሸው እና የወሰነውን ውሳኔ እንደማይቀበለው አስታወቀ። በኦነግ ከፍተኛ አመራሮች መካከል የተፈጠረውን ልዩነት ተከትሎ ምርጫ ቦርድ የአመራሮቹን ልዩነት ለመፍታትና የመጨረሻ ውሳኔ ለመስጠት ኹለቱም ቡድን የተካተቱበት ጠቅላላ ጉባኤ እንዲያካሂዱ ባሳለፍነው ታኅሳስ…

ንብረት የወደመባቸው የሻሸመኔ ነዋሪዎች የግብር እፎይታ አልተሰጠንም አሉ

በሻሸመኔ ከተማ በተፈጠሩ ግጭቶች አማካኝነት ንብረቶቻቸው ላይ ጉዳት የደረሰባቸው ነጋዴዎች የግብር እፎይታ ይሰጣቸዋል ተብለው ቃል የተገባላቸው ቢሆንም በአሁኑ ሰዓት ግን ግብር ካልከፈላችሁ ንግድ ፍቃድ ማደስም ሆነ ‹‹ክሊራንስ›› መውሰድ አትችሉም እየተባሉ እንደሆነ ሻሸመኔ የሚገኙ ጉዳት የደረሰባቸው ነጋዴዎች ለአዲስ ማለዳ አስረድተዋል። እንደ…

በትግራይ የሚገኙ ጡረተኞች ክፍያቸውን በንግድ ባንክ በኩል እንዲያገኙ ተደረገ

በደደቢት ብድር እና ቁጠባ ተቋም በኩል የጡረታ ክፍያ ይከፈላቸው የነበሩ በትግራይ ክልል የሚገኙ ጡረተኞች የጡረታ ክፍያቸውን በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እንዲከፈላቸው መደረጉን የመንግሥት ሠራተኞች ማሕበራዊ ዋስትና ኤጀንሲ ለአዲስ ማለዳ አስታወቀ። የመንግሥት ሠራተኞች ማሕበራዊ ዋስትና ኤጀንሲ ምክትል ዳይሬክተር ጥላሁን በቀለ በትግራይ ክልል…

“የማስረጃ ሕግ መዘጋጀት በፍትሕ አስተዳደር ላይ ያለውን ክፍተት ይሸፍናል” ኮሚሽነር ዳንኤል በቀለ(ዶ/ር)

የኢፌዴሪ ረቂቅ የወንጀል ሕግ ሥነ ስርዓት መሻሻሉ እና ከዚህ ቀደም ያልነበረው የማስረጃ ሕግ መውጣቱ በተጠርጠጣሪዎች ላይ የሚደርሰውን የህግ ጥሰት ይቀንስላል ሲሉ የሰብአዊ መብት ኮሚሽን ኮሚሽር ዳንኤል በቀለ ዶክተር ለአዲስ ማለዳ ተናገሩ። ከዚህ ቀደም የማስረጃ ህግ ባለመኖሩ ብዙ የሰብአዊ መብት ጥሰቶች…

ከመቀሌ አላማጣ መጓጓዣ 800 ብር ሆኗል

በትግራይ ክልል በተካሔደው የሕግ ማስከበር ዘመቻ እንቅስቃሴዎች በመገታታቸው ምክንያት ከመቀሌ አላማጣ የሚጓዙ መንገደኞች 800 ብር እየከፈሉ መሆኑን ለአዲስ ማለዳ አስታወቁ። ከመቀሌ አላማጣ የሚደርሰው መስመር ርዝመት 177 ኪሎ ሜትር ሲሆን፣ መደበኛ የታሪፍ ዋጋው 90 ብር ቢሆንም የትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጡ ተሽከርካሪዎች መንገደኞችን…

ቡለን ወረዳ በኩጅ ቀበሌ በተፈጸመው ጥቃት የተፈናቀሉ 27 ሺሕ ዜጎች የምግብ እጥረት ገጥሟቸዋል

በቤኒሻንጉል ጉምዝ መተከል ዞን ቡለን ወረዳ በኩጅ ቀበሌ ታኅሳስ 14/2013 በተፈጸመ ጥቃት ተፈናቅለው ቡለን ከተማ የሚገኙ ከ27 ሺሕ በላይ ዜጎች አስፈላጊው እርዳታ እየተደረገላቸው ባለመሆኑ በምግብ ዕጦት መቸገራቸውን ገለጹ። በንጹሓን ዜጎች ላይ በተፈጸመው ጥቃት አካባቢያቸውን ለቀው ከ20 እስከ 30 ኪሎ ሜትር…

ከአትክልት ተራ የተነሱ ነጋዴዎች የተሰጠን ስፍራ ቀድሞ በሰዎች የተያዘ ነው አሉ

ከፒያሳ አትክልት ተራ በጊዜያዊነት ወደ ጃን ሜዳ ተዛውረው የነበሩ የአትክልት እና ፍራፍሬ ነጋዴዎች ኃይሌ ጋርመንት አካባቢ የንግድ ቦታ ተሰርቶላችኋል ተብለን ከጃን ሜዳ ብንነሳም ቦታውን ማግኘት አልቻልንም ሲሉ ቅሬታቸውን ለአዲስ ማለዳ ገልጸዋል። ከመጋቢት 28/2012 ጀምረን ከፒያሳ ተነስተን ወደ ጃን ሜዳ በመሄድ…

በአንበጣ መንጋ ለተጎዱ የወረባቦ ወረዳ አርሶ አደሮች የሚቀርበው ድጋፍ ፍትሐዊ አይደለም ተባለ

በበረሃ አንበጣ መንጋ ሰብላቸው የወደመባቸው የደቡብ ወሎ ዞን ወረባቦ ወረዳ አርሶ አደሮች በመንግሥትና በበጎ ፈቃደኞች የሚቀርቡ ድጋፎች ለተጎጅ አርሶ አደሮች በእኩል እየተሰራጩ አለመሆኑን የወረዳው አርሶ አደሮች ቅሬታቸውን ለአዲስ ማለዳ አሰሙ። በወረባቦ ወረዳ ቀበሌ 17 አርሶ አደር የሆኑት መሀመድ ሲራጅ ለአዲስ…

የኢንዱስትሪ ፓርኮች ግንባታ ይቀጥላል ተባለ

በኢትዮጵያ የሚገነቡ የኢንዱስትሪ ፓርኮች ግንባታ እንደማይቆም እና ፓርኮችን መገንባቱ እንደሚቀጥል የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ለአዲስ ማለዳ አስታወቀ። ኢንዱስትሪ ፓርኮችን መንግስት አይገነባም የሚባለው መረጃ በተገቢው መልኩ ማህበረሰቡ ጋር እንዳልደረሰ መንግስት የሰራቸው ኢንዱስትሪ ፓርኮች ላይ ትኩረት ሰጥቶ እንደሚሰራ እና ሌሎችም እንደሚገነባ አስታውቋል።…

በቀጣይ 10 ዓመት ሥራ አጥነት ወደ ዘጠኝ በመቶ ዝቅ እንደሚል ተገለጸ

የኢትዮጵያ የ 10 ዓመት ብሔራዊ የልማት ዕቅድ በ2013 ተጀምሮ በ 2022 ሲጠናቀቅ ተፈፃሚ ይሆናሉ ከተባሉ የዕቅዱ ዋና ዋና ግቦች መካከል አንዱ አገራዊ የከተማ ሥራ አጥነት ምጣኔን ከ 18.7 በመቶ ወደ 9 በመቶ ዝቅ ማድረግ እንደሆነ ተጠቆመ። በኢትዮጵያ አጠቃላይ የሥራ አጥነትን…

የሞተር አልባ ተሽከርካሪዎች ረቂቅ ደረጃ እየተዘጋጀ ነው

የኢትዮጵያ ደረጃዎች ኤጀንሲ የሞተር አልባ ባለሦስት እና ባለኹለት እግር ተሽከርካሪዎች ምን ዓይነት ነገሮችን ሊያሟሉ እንደሚገባ የሚያሳይ ረቂቂ ደረጃ እየተዘጋጀ መሆኑን የኢትዮጵያ ደረጃዎች ኤጀንሲ ለአዲስ ማለዳ አስታወቀ። ይህ የሚዘጋጀው ረቂቂ ደረጃ ከዚህ ቀደም ያልነበረ ሲሆን ከአገር ውጪ የሚሰሩትንም ሆነ በአገር ውስጥ…

የሲሊንደር ጋዝ ዋጋ በኹለት ሳምንት የ350 ብር ጭማሪ አሳየ

በአዲስ አበባ የሲሊንደር ጋዝ ዋጋ በኹለት ሳምንት ውስጥ እስከ 350 ብር ጭማሪ ማሳየቱን የሲሊንደር ጋዝ የሚጠቀሙ ምግብ ቤቶች ለአዲስ ማለዳ አስታወቁ። በአዲስ አበባ ለተጠቃሚዎች ሲሊንደር ጋዝ በችርቻሮ በሚሸጡ ጋዝ ቤቶች ከኹለት ሳምንት በፊት 650 ብር ሲሸጥ የነበረ 12 ኪሎ ግራም…

ኢንቨስትመንቶች ለሚደርስባቸው ውድመት ወጥ የሆነ የካሳ መመሪያ እየተዘጋጀ ነው

የኢንቨስትመንት ፕሮጀክቶች ላይ ጉዳት ሲደርስባቸው ለደረሰባቸው ውድመት ማካካሻ የሚያገኙበት አንድ ወጥ መመሪያ የኢንቨስትመንት ኮሚሽን ከሌሎች አጋር ድርጅቶች ጋር በጋራ በመሆን እየተዘጋጀ መሆኑን የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ለአዲስ ማለዳ አስታወቀ። ከዚህ ቀደም የተለያዩ የኢንቨስትመንት ፕሮጀክቶች ላይ በተደጋገጋሚ በተለይም ከግጭቶች ጋር በተያያዘ ፕሮጀክቶች…

በኤልሻዳይ ድርጅት ታቅፈው የነበሩ ወጣቶች ወደ አዲስ አበባ እየፈለሱ ነው

በኤልሻዳይ ሪሊፍ ኤንድ ዲቨሎፕመንታል አሶሴሽን ከጎዳና ላይ ተነስተው በአፋር ክልል ካምፕ ውስጥ ከ2007 ጀምሮ ሲኖሩ የነበሩ ወጣቶች ከመስከረም ወር ጀምሮ ክፍያ እንዳልተከፈላቸው እና ለችግር እና ለረሀብ በመጋለጣቸው ወደ መሐል ከተማ እየመጡ እንዳሉ አዲስ ማለዳ ያነጋገረቻቸዉ የአይን እማኞች ተናገሩ። ታህሳስ ኹለት…

የሱር ኮንስትራክሽን ሠራተኞች የኹለት ወር ደምወዝ አልተከፈለንም አሉ

በአዲስ አበባ በሱር ኮንስትራክሽን ዋናው መሥሪያ ቤት የሚሠሩ ሠራተኞች የኹለት ወር ደምወዝ እንዳልተከፈላቸው እና ችግር ላይ እንደሆኑ ለአዲስ ማለዳ ገልጹ። አዲስ ማለዳ ያነጋገረቻቸው በመሥሪያ ቤቱ በተለያየ የኀላፊነት ቦታ የሚሠሩ ሠራተኞች ቅሬታቸውን ሲገልጹ ላለፉት ኹለት ወራት ምንም ዓይነት ክፍያ ስላልተሰጠን ችግር…

“በታጠቁ ኃይሎች ላይ የመጨረሻ የሕግ ማስከበር እርምጃ እንዲወሰድ ተወስኗል” የቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል መንግሥት ኮሙኒኬሽን ኀላፊ መለስ በየነ

በቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል መተከል ዞን ተደራጅተው በዜጎች ጥቃት የሚፈጽሙ የታጠቁ ኃይሎችን በሰላማዊ መንገድ ትጥቅ ካልፈቱ መንግሥት የመጨረሻ ሕግ የማስከበር ሥራ እርምጃ እንደሚወስድ መወሰኑን የክልሉ መንግሥት ኮሙኒኬሽን አስታወቀ፡፡ በክልሉ መተከል ዞን በተደጋጋሚ በታጠቁ ኃይሎች በንጹሐን ዜጎች ላይ ግድያ መፈጸሙን አሁንም ድረስ…

የሥጋና ወተት ኢንዱስትሪ ልማት ኢንስቲትዩት የወጪ ንግድ ገቢ በ11 በመቶ ቀነሰ

የኢትዮጵያ ሥጋና ወተት ኢንዱስትሪ ልማት ኢንስቲትዩት በ2013 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ሩብ ዓመት ከውጪ ንግድ ያገኘው ገቢ ከባለፈው ተመሳሳይ ዓመት ጋር ሲነጻጸር የ11 በመቶ ቅናሽ ማሳየቱ ተገለጸ። የኢንስቲትዩቱ የውጪ ንግድ አፈጻጸም በበጀት ዓመቱ በመጀመሪያ ሩብ ዓመት ከንዑስ ዘርፉ ምርቶች የወጪ ንግድ…

100 የዲያሊስስ ማሽኖች ወደ አገር ውስጥ ሊገቡ ነው

በያዝነው ዓመት ከኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢዎች ጋር በመሆን 100 ለኩላሊት ዕጥበት ወይንም ዲያሊስስ ሕክምና የሚያገለግሉ ማሽኖች ወደ አገር ውስጥ እንደሚያስገባ የጤና ሚኒስቴር አስታወቀ። የጤና ሚኒስቴር ከኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢዎች ኤጀንሲ ጋር በመሆን እቅድ ይዞ በዚህ የበጀት ዓመት 100 ያህል የኩላሊት ዕጥበት ሕክምና…

የወሳኝ ኹነት አገልግሎቶች ላይ የዋጋ ጭማሪ ተደረገ

በአዲስ አበባ ከተማ የመንግሥት አገልግሎት ክፍያ ማሻሻያ ከመደረጉ ጋር ተያይዞ የአዲስ አበባ ወሳኝ ኹነት ኤጀንሲ የሚሰጣቸው አገልግሎቶች ላይ የሚያስከፍለውን የአገልግሎት ክፍያ ጭማሪ መደረጉን የአዲስ አበባ ወሳኝ ኹነት ኤጀንሲ ለአዲስ ማለዳ አስታወቀ። የአዲስ አበባ ወሳኝ ኹነት ኤጀንሲ የሚሰጣቸው አገልግሎቶች ላይ የዋጋ…

የአማራ ክልል ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት ቢሮ ሦስት መመሪያዎችን አሻሻለ

የአማራ ክልል ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት ቢሮ ሦስት የኢንቨስትመንት መመሪያዎችን አሻሽሎ ማጽደቁን አስታወቀ። የተሻሻሉት መመሪያዎች መመሪያ ቁጥር 01/2013፣ መመሪያ ቁጥር 02/2013 እና መመሪያ ቁጥር 03/2013 ተብለው ሥያሜ ተስጥቷቸዋል። መመሪያ ቁጥር 01/2013 ወደ ሁለገብ ኢንዱስትሪ ፓርክ ወይም ክላስተር ማዕከል የሚገቡ የኢንዱስትሪ ፕሮጀክቶችን ለመመልመልና…

የባቢሌ ዝሆኖች መጠለያ ዳግም ክለላ ሊካሄድ ነው

በባቢሌ የሚገኙ ዝሆኖች ላይ የሚደርሰውን ሕገ ወጥ አደን እና በጫካው ላይ የሚደርሰውን ሕገወጥ ተግባራት ለመከላከል እንዲያስችል የመጠለያውን ሕጋዊ ይዞታ ለማስጠበቅ ዳግም ክለላ ሊካሄድ ግብረ ኃይል ተቋቁሞ ሥራ መጀመሩን የኢትዮጵያ ዱር እንስሳት ልማት ጥበቃ ባለሥልጣን ለአዲስ ማለዳ አስታወቀ። ከኦሮሚያ እና ሶማሌ…

የመንገድ ደህንነት ማስተግበሪያ ሕግጋት እየተዘጋጁ ነው

አዲስ አበባ ከተማ የትራንስፖርት ቢሮ እና የአዲስ አበባ ዩንቨርስቲ በጋራ በመሆን መንገድን ለተጠቃሚው ምቹ ከማድረግ አንፃር የመንገድ ደህንነት ኦዲት ማስተግበሪያ ሕግጋት እየተዘጋጀ መሆኑን አዲስ ማለዳ ያነጋገረቻቸው አዲስ አበባ የትራንስፖርት ቢሮ የሕዝብ ግንኙነት ባለሙያ ሀብታሙ ንጉሤ አስታወቁ። የመንገድ ደህንነት ኦዲት ማስተግበሪያ…

ከፍተኛ ባለሥልጣናት የመንቀሳቀሻ ፈቃድ ከጠቅላይ ሚንስትር ቢሮ እንዲይዙ መመሪያ ተላለፈ

በመንግሥት ከፍተኛ የኀላፊነት እርከን ላይ የሚገኙ ሚንስትሮች እና ዳይሬክተሮች ከሥራ ገበታቸው ላይ እያሉ በአገር ውስጥ እና በውጭ አገራት ላይ ጉዞ ለማድረግ ከጠቅላይ ሚንስትር ጽሕፈት ቤት የይለፍ ፈቃድ እንደሚያስፈልጋቸው የሚያስታውቅ ሰርኩላር መተላለፉ ታወቀ። ምንጮች ለአዲስ ማለዳ እንደገለጹት በኢትዮጵያ ውስጥ ባለው ነባራዊ…

አንገት ያስደፋው የጭካኔ ጥግ

በትግራይ ክልል ላይ እየተወሰደ ያለውን የሕግ ማስከበር እርምጃ ተከትሎ ሰባት አባላት ያሉት የአስቸኳይ ጊዜ አፈጻጸም መርማሪ ቦርድ መቋቋሙ ይታወሳል፡፡ መርማሪ ቦርዱ በመጀመሪያው ዙር የመስክ ምልከታ በባህር ዳር፣ጎንደር፣ዳንሻ፣ማይካድር እና ሁመራ ያደረገውን ምልከታ አጠናቅቆ ባለፈው ሐሙስ ሪፖርት አቅርቧል፡፡ መርማሪ ቦርዱ ከላይ በተጠቀሱት…

This site is protected by wp-copyrightpro.com